ለአበባ አምራቾች የመሬት አቅርቦት እንዲመቻች ተጠየቀ።የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር አምራቾች እና ላኪዎች ማህበር ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ ለኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ እንደተና…

ለአበባ አምራቾች የመሬት አቅርቦት እንዲመቻች ተጠየቀ።

የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር አምራቾች እና ላኪዎች ማህበር ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ ለኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ እንደተናገሩት በአሁኑ ሰአት በሀገሪቱ ያሉ የአበባ አምራቾች አጠቃላይ ይዞታ ከ1700 ሔክታር የማይበልጥ መሬት ነው፡፡

በዚህ መጠን ይዞታ ብቻ ሀገሪቱ ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከአበባ ኤክስፖርት በየአመቱ እያገኘች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አቶ ቴዎድሮስ ይህ ተጨማሪ የመሬት አቅርቦት ቢኖር የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ገቢ ምን ያህል እንደሚያሳድገው አመላካች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም መንግስት ለአበባ አምራቾች ተጨማሪ የልማት መሬት እንዲያመቻች ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል፡፡

የአበባ አምራች ዘርፍ በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ በድምሩ 200 ሺህ ለሚጠጉ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል መባሉን ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ ጽፏል፡፡

ግንቦት 07 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply