You are currently viewing ለአቶ ደመቀ መኮነን ደብዳቤ ተፃፈ! ይድረስ ለአቶ ደመቀ  መኮነን የኢትዮጵያ  መንግስት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የውጭ ጉዳይ  ሚንስትር:-የካቲት  2  ቀን 2015 አመተ ምህረት ከሰሜን…

ለአቶ ደመቀ መኮነን ደብዳቤ ተፃፈ! ይድረስ ለአቶ ደመቀ መኮነን የኢትዮጵያ መንግስት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር:-የካቲት 2 ቀን 2015 አመተ ምህረት ከሰሜን…

ለአቶ ደመቀ መኮነን ደብዳቤ ተፃፈ! ይድረስ ለአቶ ደመቀ መኮነን የኢትዮጵያ መንግስት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር:-የካቲት 2 ቀን 2015 አመተ ምህረት ከሰሜን አሜሪካ ፍሎሪዳ ግዛት ከሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ትንሣኤ አባተ ተፃፈ። የካቲት 2 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ከአለኝ ወንድምነትና ቀረቤታ አንፃር ይችን ደብዳቤ ለመፃፍ ተገደድኩ። አንድን ሰው ዝም ብሎ ከመሸሽ ነግሮ መሸሽ ይሻላል ብየ አምናለሁ። ኢትዮጵያ በነበርኩበት ወቅት አብረን ብዙ ስራዎችን ሰርተናል: የማረሳው ከልቤ የማይጠፋው ከቤተ መንግስትም ከቤተ ክህነትም ተደብቃ መገለል ደርሶባት፤ የኢትዮጵያን ታሪክ ይዛ ልትጠፋ የነበረችውን ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያምን ታሪክ ወደ ነበረ ክብሯ እንድትመለስ፤ አማራ ሳይንት ድረስ የክልሉን ባለስልጣናት ይዞ በመሄድ ለገዳሙ መንገድ እንዲሰራ በማድረገውት ሁልጊዜም ክብር እንድኖረኝ አድርጉኝ ቆይቷል። ሁኖም ግን አሁን በኢትዮጵያ በተፈጠረው ችግር ሀገር እየታመሰ ነው። የዶክተር አቢይ መንግስት ሀገራችንን ወደ ገሃነምነት እየቀየራት ይገኛል። ርሰዎት ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣን ነውት። በተለይ ሰፊውን የአማራውን ህዝብ ወክለው ነው ያሉት። አማራ እንደበግ ሲታረድ የቀብር ቦታ ተነፍጎት በዶዘር እየታረሰ ሲቀበር አንድ ቀንም ወጥተው ለአማራ ህዝብ ተናግረው ወይም ድምፀዎትን አሰምተው አያውቁም። የመጡ ሁሉ መሪዎች እርሰዎትን ምክትል እያደረጉ ለሳፕል እያስቀመጡ። ሀገር እያፈረሱ ነው። እርሰዎትም ኢትዮጵያን ለማዳን አንድ ቀንም ሲጥሩ አይታዩም። የተነቃነቀ ወበር ደጋፊ ሁነው ቀጥለዋል።ግን እስከ መቸ ራሰዎት አስበውት ያውቃሉ።በዚህ ወቅት።ፅንፈኛውና ሴረኛው ሀገር አፍራሹ የኦህዴድ ብልፅግና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት ሲከፍል ህዝብን ሲጨፈጭፍ ኢትዮጵያ የደም መሬት አኬልዳማ ስትሆን እርሰዎትም ተባባሪ ነውት? ሀገር እየመሩ የህዝብን እልቂት ማቆም ካልቻሉ በደርግ ዘመን የጎጃም ክፍለ ሀገር ገዥ የነበረ አንድ ሰው በቀይ ሽብር ተሳትፈሃል።ለብዙ ሰዎች ሞት ምክንያት ነህ ተብሎ አውሮፓ ፍርድ ቤት ቀርቦ እድሜ ልክ እንደተፈረደበት አልሰሙም? የሰው ደም ይከተላል።የብልፅግና ባለስልጣናትም ይዘገያል እጅ አንድ ቀን በህግም በእግዚአብሔርም ፊት ትጠየቃላችሁ።ኢትዮጵያን የመሰለች ታሪካዊት ሀገር አይነዎት እያየ ከመፍረሷ በፊት እንደ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ስልጣን ቢለቁ የወንድምነቴ ምክር ለመለገስ የመጀመርያ መልዕክቴን ዛሬ የካቴት 2 ቀን ይችን ደብዳቤ ልኬለዎት አለሁ ። መልክቴ እንደሚደርሰዎት ተስፋ አለኝ። ሌሎች የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ የሆናችሁ የብልፅግና አባላትም ብልፅግና ከሚባል አሸባሪ ድርጅት ውጡ በታሪክ።ተወቃሽ ከመሆናችሁ በፊት እላለሁ። ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር ሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ትንሣኤ አባተ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply