ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ይቀርብ የነበረው የስኳር ምርት መቀነሱ ተነገረ

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሰውነት አየለ ለጣቢያችን እንደተናገሩት፤ ከዚህ ቀደም በአመት እስከ 120 ሺህ ኩንታል የሚቀርበው ስኳር አሁን ከ30 ሺህ እስከ 40 ሺህ ኩንታል ብቻ ነው ብለዋል ።

በተለያዩ ምክንያቶች መጠኑ ከ120ሺህ ወደ 30 ሺህ እንደወረደ ቢያነሱም በዚህ አመት ግን እስከ 50 ሺህ ኩንታል ስኳር እየቀረበ እንደሆነም ሀላፊው ገልፀዋል።

“የሚመደብልን ስኳር በተገቢው መንገድ የማከፋፈል ስራ እንሰራለን የሚሉት” ሀላፊው፤ የመጠኑ መቀነስ ምክንያት ግን ምን እንደሆነ እንደማያቁ ተናግረዋል።

የስኳር ኮርፖሬሽን ስኳሩን እንደሚያከፋፍላቸው አንስተው ፤ የተሰጣቸውንም በአንድ መቶ ሀምሳ የሽማች ስራ ማህበራት ስኳሩን እንደሚያከፋፍሉም ገልፀዋል።

በቅርቡ በሀገሪቱ ያሉ የስኳር ማምረቻ ፋብሪካዎች በተለያዩ ምክንያቶች ስራ ማቆማቸው መዘገቡ ይታወሳል።

ለአለም አሰፋ

ሚያዚያ 01 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply