#ለአዲስ_የወለጋ_ተፈናቃዮች_የአልባሳት_ድጋፍ_ተደረገ❗️ ሸዋ ደብረብርሃን ታሕሳስ 5 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በዛሬው ቀን ደ…

#ለአዲስ_የወለጋ_ተፈናቃዮች_የአልባሳት_ድጋፍ_ተደረገ❗️ ሸዋ ደብረብርሃን ታሕሳስ 5 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በዛሬው ቀን ደብረብርሃን ከተማ በመገኜት ከወለጋ ከሞት አምልጠው በቅርብ ቀን ለመጡ ተፈናቃዮች በዱባይ ከሚኖሩ የአማራ ማህበራት እና የ ወሎ ቤተ አምሐራ – Wello Bete Amhara የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት በመተባበር 13 ጥቅል ትላልቅ ካርቶን /946 ኪሎግራም/ አልባሳት ድጋፍ ማድረግ ተችሏል። ደብረብርሃን ብቻ 6 የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፕ የሚገኝ ሲሆን ድጋፍ የተደረገላቸው ወይንሸት መጠለያ እና 08 መጠለያ ካምፕ ለሚገኙ ወገኖቻችን ነው በቦታው ተገኝተው ድጋፉን የተረከቡት የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከል የምግብ ዋስትና ዋና ሀላፊ አቶ አበባው እና ከፌዴራል የአደጋ ስጋት አመራር ተወካይ ባለሙያ አቶ አለማየሁ ፍቃዱ እና ወ/ሮ እልፍነሽ ነጋሽ በቦታው ተገኝተው ለተደረገው ድጋፍ ከልብ አመስግነዋል። የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከል የምግብ ዋስትና ዋና ሀላፊ አቶ አበባው በዞኑ 76,400 በላይ ከወለጋ ብቻ የተፈናቀሉ ወገኖች እንዳሉ ጠቅሰው ሁሉም የሀገር ውስጥ እና የውጭ እርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። የወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት ይሄ ድጋፍ እንዲሳካ በዱባይ የሚኖሩ ወገኖቻችን የሂወት ውጣ ውረድ ሳይገድበመቸው ለወገኖቻቸው ይሄንን የሰብአዊ ድጋፍ በማድረጋቸው ድጋፍ በተደረገላቸው ወገኖቻችን ስም ከልብ እናመሠግናለን። ✅-Share ወሎ ቤተ አምሐራ – Wello Bete Amhara የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት ታህሳስ 5 /2015 ዓ.ም ✅-ድጋፍ ለማድረግ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000347415891 “ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት” ብሎ ድጋፍ ማድረግ ይቻላል። መረጃውን ያደረሰን ይርጋለም ታደሠ ነው:: “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply