ለአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ለመሳተፍ የሚመጡ መሪዎች የሚያርፉባቸው ሆቴሎች መለየታቸው ታውቋል።ለ37ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ የሚሳተፍ መሪዎች የሚያርፉባቸው ሆቴሎች መለየታቸው ተገልጿል…

ለአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ለመሳተፍ የሚመጡ መሪዎች የሚያርፉባቸው ሆቴሎች መለየታቸው ታውቋል።

ለ37ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ የሚሳተፍ መሪዎች የሚያርፉባቸው ሆቴሎች መለየታቸው ተገልጿል።

የአዲስ አባበ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ለመሪዎች ማረፍያ ተብለው  ከተመረጡት ሆቴል ባለቤቶች ጋር በአግልግሎታቸው እንደዚሁም ከሰላምና ጸጥታ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች መወያያቱን ነው የገለጸው።

የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ጌታሁን አበራ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት የመሪዎች ጉባኤ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የሰላም እና የጸጥታ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

መሪዎቹ የሚያርፉባቸው ሆቴሎች ዝግጅታቸው ጨርሰው እንግዶቻቸውን እየተጠባበቁ እንደሆነ ተናግረው በሆቴሎቹ ዙርያ አዋኪ ነገሮች እንዳይኖሩ የጸጥታ አካሉ ተዘጋጅቷል ብለዋል።

ምክትል ኮሚሽነር አቶ ጌታሁን ለመሪዎች ማረፍያ ተብለው የተመረጡት ሆቴሎች የትኞቹ እንደሆኑ ግን ከመናገር ተቆጥበዋል።

የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር ፕሬዝዳት ወሮ አስቴር ሶሎሞን በበኩላቸው የህብረቱ ስብሰባ በተለያዩ ምክንያቶች ተቀዛቅዞ የቆየውን የሆቴል ኢንዱስትሪው ያነቃቃዋል ብለዋል።

ሆቴሎቹ ከመኝታ አገልግሎት ባሻገር ባህላዊና የውጪ አገር ምግቦችን በማሰናዳትና የትራንስፖርት አገልግሎቶችን በማመቻቸት የእንግዶቻቸውን ፍላጎት ለማርካት እየጣሩ እንደሚገኙ ፕሬዝዳንቷ ተናግረዋል።

በጉባኤው ተሳታፊ የሚሆኑት እንግዶች ቢያንስ አራት ምሽቶችን በአገራችን ቢያሳልፉና በእያንዳንዱ ምሽት እንግዶቹ በሚያደርጉት ወጪ የሚገኘው ገቢ ከፍተኛ መሆኑን ወ/ሮ አስቴር ገልጸዋል።

ይህም ላለፉት ሶስት ዓመታት በእጅጉ የተጎዳውን የሆቴል ኢንዱስትሪ ማገገም እንዲችል ያደርገዋል ብለው ያምናሉ።

የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ለመዘገብ ከ1ሺህ በላይ የተለያዩ አገራት ጋዜጠኞች ወደ አገራችን እንደሚገቡ ከሰሞኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መግለጹ ይታወሳል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

የካቲት 07 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply