
ከአራት ዓመት በፊት ለደረሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737-ማክስ 8 አደጋ ምክንያት የቦይንግ የበረራ መቆጣጠሪያ ሥርዓት ችግር መሆኑን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር አስታወቀ። ለ157 ሰዎች ህልፈት የሆነው የበረራ ቁጥር ኢቲ 302ን አደጋ አስመልክቶ ሚኒስቴሩ ሲካሄድ የነበረው ምርመራ የማጠቃለያ ሪፖርቱን ዛሬ ታኅሣሥ 14/2015 ዓ.ም. ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው ይህንን ያሳወቀው።
Source: Link to the Post