ለኦነግ የሚሰራ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል አባላት በቁጥጥር ስር ዋለ።                 አሻራ ሚዲያ          ህዳር፡-14/03/13/ዓ.ም ባ…

ለኦነግ የሚሰራ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል አባላት በቁጥጥር ስር ዋለ። አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-14/03/13/ዓ.ም ባ…

ለኦነግ የሚሰራ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል አባላት በቁጥጥር ስር ዋለ። አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-14/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር ለኦነግ የሚሰራ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል አባላት የሆነው ቶላ ሆራ በቁጥጥር ስር ውሏል። በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ኤልዋየን ወረዳ ቶላ ሆራ የሚባል የኦነግ ሸኔ ወታደር ለውጡን ተከትሎ የኦሮሚያ ልዩ ሃይልን ተቀላቅሎ ሲሰራ እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ይህ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል አባል ሆኖ በመስራት ላይ ያለው ቶላ ሆራ ለረጅም ጊዜ ለኦነግ ሸኔ ወታደሮች ሚስጥር በማውጣት ሲሰራ መቆየቱም ተገልጻል፡፡ ከሁለት ቀን በፊት የራሱን እና የጓደኛውን ክላሽ በመያዝ የኦነግ ሸኔ ወታደሮችን ለመቀላቀል በጉዞ ላይ ሳለ ዛሬ ሰኞ, ሕዳር-14-2013 በሕብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል። የአካባቢው ነዋሪወች እንደገለጹት የኦሮሚያ ልዩ ሃይል አባል የሆኑ ነገር ግን ከኦነግ ጋር እየተመሳጠሩ ይህን መሰል ድርጊት የሚሰሩ የሚሰሩ እንዳሉም ተናግረዋል፡፡ ስለሆነም የኦሮሚያ መንግስት በስሩ ያሉትን አመራሮችና የልዩ ሃይል አባላት ሊፈትሽ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply