You are currently viewing “ለከተማችን ህዝብ ሁለንተናዊ ደህንነት ሲባል በሰዓት የተገደበ የተሽከርካሪና የሰው የእንቅስቃሴ ገደብ ተቀምጧል።” የደሴ ከተማ አስተደደር! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…     ነሀሴ 4 ቀ…

“ለከተማችን ህዝብ ሁለንተናዊ ደህንነት ሲባል በሰዓት የተገደበ የተሽከርካሪና የሰው የእንቅስቃሴ ገደብ ተቀምጧል።” የደሴ ከተማ አስተደደር! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ነሀሴ 4 ቀ…

“ለከተማችን ህዝብ ሁለንተናዊ ደህንነት ሲባል በሰዓት የተገደበ የተሽከርካሪና የሰው የእንቅስቃሴ ገደብ ተቀምጧል።” የደሴ ከተማ አስተደደር! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ነሀሴ 4 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከደሴ ከተማ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ!! የደሴ ከተማ አስተዳደር ወቅታዊውን የጠላት እንቅስቃሴ መሠረት በማድረግ በርካታ ስራዎችን ሲሰራ የቆየ መሆኑ ይታወቃል። ነባራዊው የከተማችን ሁኔታ ከወትሮው በተለየ የከተማችንን ህዝብ ልዩ ክትትልና ድጋፍ የሚጠይቅ ነው። በከተማችን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተፈናቃይ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የሀይማኖት ተቋማትን ጨምሮ ከልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሠራት ላይ ይገኛል። ሆኖም ለከተማችን ህዝብ ሁለንተናዊ ደህንነት ሲባል በሰዓት የተገደበ የተሽከርካሪና የሰው የእንቅስቃሴ ገደብ ተቀምጧል። 1ኛ. መላ የከተማችን ነዋሪዎች ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ ከተፈቀደላቸው የፀጥታ አካላት ውጭ የትኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ የተከለከለ ነው። 2ኛ.ከተፈቀደላቸው የፀጥታ ተቋማትና የጤና ተቋማት ተሽከርካሪዎች ውጭ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እንቅስቃሴአቸው እንዲገደብ ተወስኗል። 3ኛ. የሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ብቻ እንዲሆን የተወሰነ መሆኑን እናሳውቃለን። ይህ ውሳኔ ከዛሬ ነሀሴ 04/2013 ዓ.ም ጀምሮ በከተማችን ተግባራዊ ይደረጋል። መላ የከተማችን ነዋሪዎችም በተለመደው አግባብ ለሁሉን አቀፍ ትብብር እራሳችሁን ታዘጋጁ ዘንድ የደሴ ከተማ አስተዳደር ጥሪውን አቅርቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply