
ትግራይ ውስጥ ሲካሄድ በነበረው ጦርነት ውስጥ ተሳትፎ የነበራት ኤርትራ ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ጦርነቱ ማገርሸቱን ተከትሎ የተጠባባቂ ጦር አባላቷን በመጥራት ወደ ጦሩ እንዲቀላቀሉ አድርጋ ነበር። ጦርነቱ እንዲቆም ያደረገው የሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ እነዚህ የአገሪቱ ተጠባባቂ ጦር አባላት ወደ ቤታቸው አየተመለሱ መሆናቸውን ቢቢሲ ከሠራዊቱ አባላት እና ከቤተሰባቸው ለማረጋገጥ ችሏል።
Source: Link to the Post