ለኮምቦልቻ እና ለደሴ ሆስፒታሎች የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ድርጅት አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም አዲ…

ለኮምቦልቻ እና ለደሴ ሆስፒታሎች የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ድርጅት አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ድርጅት በአሸባሪዎችና ወራሪዎች ጉዳት በደረሰባቸው የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ለተጎዱ በርካታ ወገኖችና ለተቋማት ጭምር ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል። በጎ አድራጎት ድርጅቱ በአሸባሪዎች ይፋዊ ጦርነት እና ዝርፊያ ከተፈጸመባቸው አካባቢዎች መካከል ወደ ደሴ እና ኮምቦልቻ በማቅናት ለተጎዱ ሆስፒታሎች ድጋፍ ማድረጉን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ድርጅት በቅርብ ግዜ ተመርቆ ወደ ስራ የገባው የኮምቦልቻ ሆስፒታል በብዙ ሚሊየን ብር የተገዙ አዳዲስ የነበሩ የሆስፒታሉ የህክምና መስጫ መሳሪያወች እና መድሀኒት በአሸባሪው ትሕነግ ሙሉ ለሙሉ መዘረፉን እና የተቀረው ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን አውስቷል። ለመጀመሪያ የህክምና እርዳታ እንዲሁም ለወላድ እናቶች የሚሆን መድሀኒት በሚል 150,000 ብር /አንድ መቶ ሀምሳ ሺ ብር/ ወጭ በማድረግ በወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት የቦርድ አባል እና የድርጅቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ በሆኑት በዶክተር አብዱ ይማም /በኮምቦልቻ ሆስፒታል ሀኪም / በባለሙያ የተገዛ ለደሴ ሆስፒታል እና ለኮምቦልቻ ሆስፒታል በአጠቃላይ 300,000 ብር /ሶስት መቶ ሺ ብር / ማህበሩ ወጭ በማድረግ ጉዳት ለደረሰባቸው የህዝብ መገልገያ እገዛ ተደርጓል ብሏል። የኮምቦልቻ ሆስፒታል ዋና ሀላፊ አቶ ከበደ ለተደረገው ድጋፍ ከልብ አመስግነው ሁሉም ኢትዮጵያዊ የተቻለውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። በተመሳሳይ በደሴ ከተማ በመገኜት በከፍተኛ ሁኔታ የወደመውን የደሴ ሆስፒታል በመመልከት ለመጀመሪያ የህክምና እርዳታ እና ለወላድ እናቶች የሚሆን ግምቱ 150,000 ብር /አንድ መቶ ሀምሳ ሺ ብር/ የሚሆን የመድሀኒት እገዛ ማድረጉ ተወስቷል። ለተደረገው እገዛም የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ልኡል ከልብ አመስግነው ሆስፒታሉ በአመት ለግማሽ ሚሊዮን ህዝብ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ የ80 አመት እድሜ ያለው አንገፋ የህዝብ መገልገያ ተቋም በጁንታው ሀይል 1.2 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሀብት የተዘረፈ እና የወደመ መሆኑን ገልፀው ሁሉም ኢትዮጵያዊ እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ ስለማቅረባቸው ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ድርጅት አስታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply