ለወራት ደመወዝ የተቋረጠባቸው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች መቸገራቸውን ገለጹ

https://gdb.voanews.com/01000000-0a00-0242-eee8-08db7998c290_tv_w800_h450.jpg

የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች፥ “የሁለት ወር ደመወዛችን ስላልተከፈለን፣ ከነቤተሰቦቻችን ለችግር ተዳርገናል፤” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን የሚገኘው ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሥራ ያቆመው፣ እአአ ግንቦት 20 ቀን 2023 እንደነበር ያስታወሱት ሠራተኞቹ፣ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አካባቢውን ተቆጣጥሮ በነበረበት ወቅት በደረሰበት ጉዳት፣ ፋብሪካው እስከ አሁን ሥራ አለመጀመሩን አክለው ገልጸዋል።

ሠራተኞቹ ለአሰሙት ቅሬታ፣ ከፋብሪካው አመራሮች መልስ ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረግነው ጥረት፣ ለዚኽ ዘገባ አልተሳካም። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ፣ መረጃው እንዳለው ገልጾ፣ ፋብሪካው ወደ መደበኛ ሥራው በሚመለስበት እና የሠራተኞች ደመወዝ በሚከፈልበት ኹኔታ ላይ ምክረ ሐሳብ አቅርቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply