ለዋግኽምራ ፃግብጂ ፋኖዎች የአልባሳት ድጋፍ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 2 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የጀግኖቹ ልጆች የዋግ ሹሞቹ ሀገር የትግራይ ወራሪ…

ለዋግኽምራ ፃግብጂ ፋኖዎች የአልባሳት ድጋፍ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 2 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የጀግኖቹ ልጆች የዋግ ሹሞቹ ሀገር የትግራይ ወራሪ ሀይልን ብቻቸውን ከ6 ወር በላይ የተዋጉት የፃግብጂ ፋኖ እና ሚሊሻ የጀግንነት ታሪክ የሚደንቅ ስለመሆኑ ተገልጧል። የወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ድርጅት ደግሞ በዋግኽምራ ሰቆጣ ከተማ በመገኘት ትልቅ የተጋድሎ ጀግንነት ለፈፀሙት ለፋኖ እና ለሚሊሻ አባላት 70,000 ብር /ሰባ ሺ ብር / ወጭ በማድረግ 75 ሬንጀር ሱሪ እና 75 ሬንጀር ቲሸርት ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል። በተመሳሳይም ማህበሩ ለአረጋውያን እመጫት እና ነፍሰጡር በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ሰቆጣ ከተማ ለ400 አባዎራ 450,000 ብር ወጭ የተደረገበት 100 ኩንታል ዱቄት ድጋፍ ማድረጉን ገልጧል። ዋግ ሹሞቹ አገር በማፅናት እና በመጠበቅ ረገድ ከቅድመ አያቶቻቸዉ የወረሱትን የአርበኝነት ቃል ኪዳን ሳይሸራርፉ ሊገድል፣ ሊዘርፍና ሊያወድም አልሞ የመጣዉን የትግራይ ወራሪ ሓይል፣ የአባቶቻቸውን የነ ዋግ ሹም ጓንጉልን፣ ጄኔራል ሃይሉ ከበደን ታሪክ በመድገም አኩሪ ጀብድ ፈፅመዋል ብሏል ድጋፉን ያበረከተው ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ድርጅት። ዋግኽምራ በአማራ ክልል የሚገኝ በቀድሞው የወሎ ክፍለ ሀገር የዋግ አውራጃ ሲሆን ካሉት 11 ወረዳዎች በሽምቅ ዉጊያ ጠላትን ድባቅ በመምታት ምድራቸውን እንዳያረክስ፣ ታሪክቸዉን እንዳያጎድፍ ያደረጉ ናቸው። በተለይም የሰሀላ ሠየምት፣ የድሃና፣ የዝቋላ፣ የአበርገሌ እና የጻግብጂ ወረዳ ሚሊሻዎችና ፋኖዎች የሰሩት ጀብድ በታሪክ መዝገብ ሲታወስና ሲዘከር የሚኖር ገድል ስለመሆኑ ገልጾ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ያሰፈረው ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ድርጅት ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply