ለውድ የባንካችን ደንበኞች በሙሉ መረጃን ወቅታዊ የማድረጊያ ቀነ ገደብ ለሁለት ወራት ተራዘመ

ለውድ የባንካችን ደንበኞች በሙሉ መረጃን ወቅታዊ የማድረጊያ ቀነ ገደብ ለሁለት ወራት ተራዘመ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብሔራዊ ባንክ እ.ኤ.አ በ27/08/2021 ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ ላለፉት 6 ወራት የደንበኞቹን መረጃ የማደራጀትና የማጥራት ስራ ሲሠራ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
በዚህ ጊዜ ውስጥ በርካታ ደንበኞች መረጃቸውን በባንኩ ቅርንጫፎች በመገኘት ወቅታዊ አድርገዋል፡፡
በተለያዩ ምክንያቶች መረጃቸውን ወቅታዊ ማድረግ ላልቻሉ ደንበኞች ተጨማሪ የሁለት ወር ጊዜ የተሰጠ በመሆኑ፣ ደንበኞች ቀነ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት ከወዲሁ ወደ ባንኩ ቅርንጫፎች በመሄድ መረጃቸውን ወቅታዊ ማድረግ እንዳለባቸው እናሳስባለን፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply