“ለውጥ መጣ ከተባለ ማግሥትም “ፀረ አማራ ትርክቱና ግድያዉ ቀጥሏል፤ በአሁኑ ወቅትም በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የአማራዉ የደም ጎርፍ እየፈሰሰ ነው”” የአማራ ዴሞክራሲ ኃይሎች ን…

“ለውጥ መጣ ከተባለ ማግሥትም “ፀረ አማራ ትርክቱና ግድያዉ ቀጥሏል፤ በአሁኑ ወቅትም በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የአማራዉ የደም ጎርፍ እየፈሰሰ ነው”” የአማራ ዴሞክራሲ ኃይሎች ን…

“ለውጥ መጣ ከተባለ ማግሥትም “ፀረ አማራ ትርክቱና ግድያዉ ቀጥሏል፤ በአሁኑ ወቅትም በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የአማራዉ የደም ጎርፍ እየፈሰሰ ነው”” የአማራ ዴሞክራሲ ኃይሎች ንቅናቄ (አዴኃን) ሊቀ መንበር አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 8 ቀን 2013 ዓ.ም… አዲስ አበባ ሸዋ አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ የአማራ ዴሞክራሲ ኃይሎች ንቅናቄ (አዴኃን) ሊቀ መንበር ከበኩር ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ አማራዉ ለዘመናት ሲጨፈጨፍ የቆየዉ በተሠራበት የሀሰት ትርክት ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል። ቀደም ሲል አማራዉ የተደረገበትን ግፍ በመረዳትም ከዓመታት በፊት ጀምሮ በትጥቅ ትግል አማራዉ የሚደርስበትን መዋቅራዊ የዘር ማጽዳት ሤራ ሲታገሉ መቆየታቸዉን አስታውሰዋል። ለውጥ መጣ ከተባለ ማግሥትም “ፀረ አማራ ትርክቱና ግድያዉ ቀጥሏል፤ በአሁኑ ወቅትም በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የአማራዉ የደም ጎርፍ እየፈሰሰ ነው” ብለዋል። ድርጊቱንም “ለአማራዉ ወርቅ ላበደረ ጠጠር” ገጥሞት በየሄደበት እየታረደ ነው” ሲሉ ገልጸውታል። አቶ ተስፋሁን አያይዘውም ሌሌች የፖለቲካ ኃይሎች የሚከተሉት እሳቤ ፀረ አማራ ርዕዮት ዓለም መሆኑን አስገንዝበዋል። በመሆኑም “አማራዉ ሲጨፈጨፍ በስሙ ጠርተዉ እንኳ ለማውገዝ አይፈልጉም” ብለዋል። አማራዉ የሚደርስበትን ጭፍጨፋ ለማስቆም መዋቅራዊ ለውጥ እንደሚያስፈልግ የተናገሩት አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ “ሕገ መንግሥቱ አማራዉን ሀገር አልባ አድርጎታል፤ ይህን የለቅሶ ፖለቲካ ለማስቆምም እየታገልን ነው፤ መራራ ትግል በማድረግም ከዚህ ደርሰናል” ብለዋል። ህወሓት ላይመለስ ወደ መቃብር ወርዷል። ነገር ግን ጥሎት ያለፈዉ ፀረ አማራ ትርክቱ አልተለወጠም። የዚህ ትርክት ውጤት ደግሞ የአማራዉ ደም እንደ ጎርፍ እየፈሰሰ እንዲቀጥል አድርጓል። “እጅግ የሚያሳዝነው” አሉ አቶ ተስፋሁን ‘በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ’ እንደሚባለዉ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ለውጥ እናመጣለን የሚሉ ኃይሎች (የፖለቲካ ፓርቲዎች) ሳይቀር አማራዉ በማንነቱ እየተገደለ በስሙ ጠርተዉ ዘር ማጥፋትን ለማውገዝ ይዳዳቸዋል፤ ይህ አጉል መመፃደቅና የፀረ አማራ ትርክቱ ሰለባነታቸዉ ውጤት ነው፣ የምናስታምመዉ ጉዳይ አይደለም” ብለዋል። ስለዚህ ችግሩን በሚገባ በመረዳት እንደ ችግሩ ጥልቀት መፍትሔ መስጠት እንደሚገባ በመጠቆም ችግሩን በማለባበስ ከቀጠለ ግን እንደሚያባብሰው ተናግረዋል። አቶ ተስፋሁን እንዳሉት የፀረ አማራ ትርክቱ ሰለባዎች በመንግሥትም በተቃዋሚ ኀይል ጎራዎችም ይገኛሉ። እነዚህ ኀይሎች ደግሞ አማራዉ እንዲገደል የሚያደርጉ ናቸው። ችግሩን ለማስቆም ደግሞ ንቅናቄዉ መራራ ትግል እያደረገ ይገኛል ነው ያሉት። ንቅናቄዉ አማራዉ የሚደርስበትን ግፍ ለማስቆም ከዓመታት በፊት የትጥቅ ትግል ሲያደርግ ቆይቷል። ከለውጡ ማግሥት ደግሞ በሰላማዊ መንገድ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ በሰላማዊ መንገድ እየታገለ ይገኛል። አማራዉ የሚደርስበትን ግፍም በተደጋጋሚ በመግለጫዎችና በሌሎች የመገናኛ ዘዴዎች ሲያወግዝ መቆየቱን ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም በቂ ባይሆንም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድርጊቱን እንዲያዉቀዉ መሥራታቸዉን አመልክተዋል። ይሁን እንጂ “ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም የፀረ አማራ ትርክቱ ሰለባ ነውና እውነቱ እስኪታወቅና ችግሩ መፍትሔ እስኪያገኝ አጠናክረን እንቀጥላለን” ብለዋል። እንደ አቶ ተስፋሁን ማብራሪያ ገለልተኛ ወገን ችግሩን ማጣራት አለበት፤ ይህ እንዳለ ሆኖ አማራዉም ችግሩን በትግል ማሸነፍ አለበት። አማራዉ በህይወት የመኖር መብቱን እንዲያስከብር መታገል ይገባዋል። ንቅናቄዉም ከዚህ ቀደም የጀመረዉን የአማራዉን ኅልውና የማስጠበቅ ትግል በሰላማዊ መንገድ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። “ኢትዮጵያን የሚወድና ኢትዮጵያን ለመታደግ ፍላጎት ያለዉ ሁሉ የአማራን ትግል ይደግፍ፣ የአማራዉ ትግል የኢትዮጵያ ትግል ነውና። አማራዉ የሚደርስበትን የዘር ማጽዳት ማሽሞንሞን ሳይሆን በግልጽ በስሙ ጠርተዉ ያውግዙ” በማለት ጥሪ አቅርበዋል። በኩር ጋዜጣን ጠቅሶ አዴኃን እንዳጋራው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply