You are currently viewing “ለዐቃቤ ህግ የውሳኔ መስጫ ግዜ የተሰጠው 15 ቀናት አቃቤ ህግ በችሎት ቀርቦ ጥያቄ አቅርቦ የተሰጠው ሳይሆን ተከራካሪወች ብይን እስኪሰጥ ለመጠባበቅ በወጡበት በቢሮ በኩል ጠይቋል በሚል የተ…

“ለዐቃቤ ህግ የውሳኔ መስጫ ግዜ የተሰጠው 15 ቀናት አቃቤ ህግ በችሎት ቀርቦ ጥያቄ አቅርቦ የተሰጠው ሳይሆን ተከራካሪወች ብይን እስኪሰጥ ለመጠባበቅ በወጡበት በቢሮ በኩል ጠይቋል በሚል የተ…

“ለዐቃቤ ህግ የውሳኔ መስጫ ግዜ የተሰጠው 15 ቀናት አቃቤ ህግ በችሎት ቀርቦ ጥያቄ አቅርቦ የተሰጠው ሳይሆን ተከራካሪወች ብይን እስኪሰጥ ለመጠባበቅ በወጡበት በቢሮ በኩል ጠይቋል በሚል የተሰጠ ነው።” አስረስ ማረ ዳምጤ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ፖሊስ ተጨማሪ 14 ቀናት ለምርመራ ማጣሪያ እንዲሰጠው የተለመደ ጥያቄውን አቅርቧል። የዘመነ ካሴ ጠበቆች በሙሉ ታደሰ፣ ሕሩይ ባዩ እና አዲሱ ጌታነህ ተጨማሪ ግዜ ቀጠሮ መሰጠት የለበትም የሚሉባቸውን ዝርዝር ምክንያቶች አቅርበው ተከራክረዋል። ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ 14 ቀናት ውድቅ በማድረግ መዝገቡን የዘጋው ቢሆንም ዐቃቤ ህግ በግዳዩ ላይ ውሳኔ እንዲሰጥ ወይም በተለምዶ የክስ ማዘጋጃ ግዜ የሚባለውን 15 ቀናት በመስጠት መዝገቡን ዘግቶታል። ሆኖም ይህ ለዐቃቤ ህግ የውሳኔ መስጫ ግዜ የተሰጠው 15 ቀናት አቃቤ ህግ በችሎት ቀርቦ ጥያቄ አቅርቦ የተሰጠው ሳይሆን ተከራካሪወች ብይን እስኪሰጥ ለመጠባበቅ በወጡበት በቢሮ በኩል ጠይቋል በሚል የተሰጠ ነው። የዐቃቤ ሕግ ለችሎቱ አቀረበዉ የተባለዉ ጥያቄ ለጠበቆች ሳይደርስ በሚያስፈልገው የግዜ መጠን ላይም ክርክር ሳይደረግ ፍርድ ቤቱ በራሱ ግዜ 15 ቀን መስጠቱ ከፍርድ ቤቱ የማይጠበቅ ብይን እና የችሎት አመራር ነው። የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የግዜ ቀጠሮ መዝገብ በዚህ ሁኔታ የተጠናቀቀ ሲሆን የምርመራ ቡድኑ ቀዳሚ ምርመራ አደርጋለሁ በሚል ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እና መጥሪያ ዘመነን ወደ ባህርዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት አቅርበዉታል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply