ለዓለም አቀፍ ማህረሰብ ጥሪ የቀረበ ሰላማዊ ሰልፍ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ነው፡፡በዛሬው ዕለት በአቢ አዲ ከተማ የሚገኙ ተፈናቃይ ዜጎች ወደ ቀያችን መልሱን፣የፕሪቶሪያው የሰላም ስ…

ለዓለም አቀፍ ማህረሰብ ጥሪ የቀረበ ሰላማዊ ሰልፍ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ነው፡፡

በዛሬው ዕለት በአቢ አዲ ከተማ የሚገኙ ተፈናቃይ ዜጎች ወደ ቀያችን መልሱን፣የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ይከበር ሲሉ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡

ከሰሞኑ በተለያዩ የትግራይ ክልሎች ሰላማዊ ሰልፎች ሲካሄዱ መቆየታቸውን የሚታወቅ ሲሆን በአዲግራት፣ሽሬ፣አክሱም እና መቀሌ ከተሞች ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡

በዛሬው ዕለትም በአቢ አዲ ከተማ የሚገኙ ተፈናቃይ ዜጎች ሰላማዋ ሰልፍ በማድረግ የአለም አቀፍ ማህበረሰቡን ዕርዳታ ጠይቀዋል፡፡

በሰልፉ ላይ ተሳትፎ የነበራቸው በአቢ አዲ ፕሪፓራቶሪ መጠላያ ካምፕ ነዋሪ የሆኑት አቶ ብርሃነ ለጣብያችን እንደተናገሩት በዛሬው ዕለት በነበረው ሰልፍ ላይ ወደ ቀያችን መልሱን፣ልመና ይብቃን፣ህገ-መንግስቱ ይከበር እና ሰብዓዊ እርዳታ ይገባልን የሚሉ ጥያቄዎች እንደነበሩ ነግረውናል፡፡

ጥያቄያችንን የሚሰማ የፌደራል መንግስትም ሆነ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥሪያችንን በመስማት ይድረስልን ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በትግራይ ክልል ከሰሞኑን ተመሳሳይ ሰልፎች እየተካሄዱ ሲሆን ቀጣይነት ሊኖራቸው እንደሚችልም ይገመታል፡፡

በትላትናው ዕለት በመቀሌ በነበረው ሰልፍ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ግዚያዊ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ “እዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የወደቃችሁት ሥራችንን መሥራት ስላልቻልን ነው ” ማለታቸውን ይታወሳል፡፡

አቤል ደጀኔ
ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply