“ለዓመታት ስናቀርባቸው የነበሩ መሰረታዊ ጥያቄዎች በመንግስት በኩል እልባት ያልተሰጣቸው በመሆናቸውና እስካሁንም እየተንከባለሉ ለመቆየታቸው ተጠያቂው የትምህርት አመራሩ እንደሆነ በአፅንኦት እ…

“ለዓመታት ስናቀርባቸው የነበሩ መሰረታዊ ጥያቄዎች በመንግስት በኩል እልባት ያልተሰጣቸው በመሆናቸውና እስካሁንም እየተንከባለሉ ለመቆየታቸው ተጠያቂው የትምህርት አመራሩ እንደሆነ በአፅንኦት እናምናለን።” የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ህዳር 26 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከህዳር 26 ጀምሮ ስለሚካሄደው የስራ ማቆም አድማ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች የአቋም መግለጫ! የአሶሳ ዩንቨርሲቲ መምህራን ከሌሎችም የኢትዮጵያ ዩንቨርሲቲዎች በተለየ መልኩ ከአሉበት ፈርጀ ብዙ ችግሮች አኳያ በመደራጀት እና ጥያቄዎችን በተደራጀ መንገድ ማቅረብ ከጀመረ ውሎ አድሯል። የስራ ማቆም አድማን ጨምሮ ሌሎች ተቃውሞዎችን እንደሚያደርግም ከወራት በፊት ከ 430 በላይ አባላቱ የፈረሙበትን Petition ለሚመለከተው ሁሉ አስገብቷል። ሆኖም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገውን የስራ ማቆም አድማ በሙሉ ልብ ተግባራዊ እንዲደረግ የድርሻውን ይወጣል። ከዚህ በታች የተገለፁት ነጥቦች የአቋም መግለጫዎቻችን ናቸው። 1. ለአመታት ስናቀርባቸው የነበሩ መሰረታዊ ጥያቄዎች በመንግስት በኩል እልባት ያልተሰጣቸው በመሆናቸውና እስካሁንም እየተንከባለሉ ለመቆየታቸው ተጠያቂው የትምህርት አመራሩ እንደሆነ በአፅንኦት እናምናለን። ለመምህራን ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የዘገየው የአመራር ቡድን ለትምህርት ጥራት መጓደል ሙሉ የታሪክ ተጠያቂ እንዲሆን እንጠይቃለን። የመኖር ሰብዓዊ መብታችን ለማስከበር ማንኛውንም ሰላማዊ የትግል ስልት የምንከተል መሆኑንም እንገልፃለን። 2. ከህዳር 26 ጀምሮ የሚካሄደውን የስራ ማቆም አድማ ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመነጋገር ፣ ጥያቄያችን ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ አድማው በዩኒቨርሲቲያችን የሚቀጥል መሆኑን እየገለፅን አስተዳደራዊ ሀላፊነት ያለባችሁ መምህራን ምንም አይነት የመማር ማስተማር ስራ ላይ መሰማራት ከመምህራን ትግል ጋር የሚጋጭ መሆኑን እንገልፃለን። 3. የመምህራን ማህበርን ጨምሮ ሌሎች ዩንቨርሲቲዎች እና ግለሰቦች ከዚህ ትግል ተቃራኒ የመቆማቸው ዋና ምክንያት ፖለቲካዊ አልያም ሌላ አድርባይነት መሆኑን በአንፅዖት ስለምንረዳ ሌሎች ተስፋ የሚጣልባቸው ተቋማት እና መምህራን የመምህራን ትግል የመኖር ያለመኖር ጉዳይ መሆኑን ከግምት በማስገባት ተባባሪ እንዲሆኑ በድጋሚ እንጠይቃለን። 4. የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን እና የሙያ ረዳቶቻቸው በየትኛውም የመምህራን ማህበር መቋቋሚያ ጉባኤ ላይ በህጋዊ ውክልና ተገልፀው ተወካይ የሌላቸው በመሆኑ ከሁሉም ዩንቨርስቲዎች የተሰባሰቡ መምህራን ጥያቄያችንን ወክለው የመንቀሳቀስ ሙሉ ውክልና የተሰጣቸው መሆኑን እንገልፃለን። 5. ማንኛውም የሚዲያ አካልም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲ የጥያቄዎቻችንን ዝርዝር ባለማወቅም ይሁን ሆነ ብሎ ያልሆነ ገፅታ ለመስጠት መጣር ከሀቅ መጋፈጥ መሆኑን እንገልፃለን። በመጨረሻም የስራ ማቆም አድማው የሀገር አቀፍ ንቅናቄው ጋር በመናበብ የሚደረግ በመሆኑ ለዚህም ተከታታይ መረጃዎችን የምናደርስ መሆኑን እየገለፅን መላ አባላቶቻችን እና ደጋፊዎቻችን ከእናንተ ጋር ይህን ታሪካዊ ሀላፊነት እንደምንወጣ በመተማመን ነው ። መምህርነት የሙያዎች ሁሉ አባት ነው ። አሶሳ _ኢትዮጵያ

Source: Link to the Post

Leave a Reply