ለዓመታት ደክመን በተመረቅንበት ሙያ ራስን፣ ቤተሰብን፣ ህዝብን ብሎም ሀገርን ለማገልገል ዝግጁ ብንሆንም በጀት የለም በሚል ምክንያት ባለመመደባችን አላግብብ እየተጉላላን ነው ሲሉ የህክምና ባ…

ለዓመታት ደክመን በተመረቅንበት ሙያ ራስን፣ ቤተሰብን፣ ህዝብን ብሎም ሀገርን ለማገልገል ዝግጁ ብንሆንም በጀት የለም በሚል ምክንያት ባለመመደባችን አላግብብ እየተጉላላን ነው ሲሉ የህክምና ባ…

ለዓመታት ደክመን በተመረቅንበት ሙያ ራስን፣ ቤተሰብን፣ ህዝብን ብሎም ሀገርን ለማገልገል ዝግጁ ብንሆንም በጀት የለም በሚል ምክንያት ባለመመደባችን አላግብብ እየተጉላላን ነው ሲሉ የህክምና ባለሙያዎች ቅሬታ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማራ ክልል የሚገኙ ጠቅላላ ሀኪሞች ከምደባ መዘግየት ጋር በተያያዘ እያጋጠመን ያለው ችግር እየተፈታ ባለመሆኑ ለከፋ ፈተና ተዳርገናል ሲሉ ቅሬታቸውን ለአሚማ አስታውቀዋል። ዶ/ር መሀሪ እንዳላማው ይባላል፤ በአማራ ክልል ለጊዜው ስራ ፈላጊ ሀኪም ሲሆን በ2012 ዓ.ም በህክምና ሳይንስ ከተመረቁ ዶክተሮች መካከል አንዱ ነው። ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ይፋ በተደረገው አሰራር መሰረት በክልል ደረጃ ምደባ እንዲሰጠን ብንጠይቅም ምላሽ አላገኘንም ብሏል። የጤና ተቋማት ክፍት እና የሰው ሀይል የሚያስፈልጋቸው ቢሆንም እኛ አሁን እናንተን ለመቅጠር የሚያስችል በጀት የለንም የሚል ምላሽ የሰጡን በመሆኑ ላለፉት 8 ወራት እቤታችን ለመቀመጥ ተገደናል፤ ቁጥራችንም ከ300 በላይ እንሆናለን ነው ያለው። በዚህምሀገራችንን፣ቤተሰባችንን ብሎም ራሳችንን መጥቀም አልቻልንም፤ 7 ዓመት ተምረን ያለ ስራ እየተጉላላን እንገኛለን ሲል አክሏል። ክልሉ በጀት ከሌለው ለምን ሌላ አማራጮችን አይሰጠንም? ያለው ዶ/ር መሀሪ ካልሆነ ወደ ጎረቤት ሀገር ሄደን የምንሰራበትን ሁኔታ እንዲያመቻችልን እንጠይቃለን ብሏል። የአብክመ ጤና ቢሮ ከሀምሌ ጀምሮ ለ2013 የሚለቀቀው በጀት አልተፈቀደልኝም በማለቱ ርዕሰ መስተዳድር አማካሪን ስንጠይቅ የችግሩን አሳሳቢነት ተረድተው እንደ ሀገርም እንደ ክልልም ተወያይተን እናሳውቃችኋለን ቢሉም አልተሳካም ሲል ገልጧል። የሙያ ፈቃድ ሲኦሲ ፈተና ወስደን የሙያ ፈቃድ ከያዝን በኋላም ይህን ያህል መጉላላት ተገቢ አይደለም ያለው ዶ/ር መሀሪ ጥያቄያችን አለመመለስ በዘርፉ ለመሰማራት የሚፈልጉ የትውልዱን አካላት ተስፋ ማጨለም ይሆናል ብሏል። የህክምና ትምህርት በራሱ በየጊዜው ካልሰራህበት የሚረሳና ተግባራዊ ልምምድን የሚፈልግ ሙያው በመሆኑ ትኩረት እንዲሰጠው ተጠይቋል። ዶ/ር አቤኔዘር በበኩሉ የቅጥር ሁኔታችን ወደ ከልል በመዞሩ በተለይ በአማራ ክልልና በአዲስ አበባ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆን ዶክተሮች በሌሎች አካባቢዎች የመቀጠር ዕድላችን እየጠበበ በመምጣቱ አሰራሩ ሊፈተሽ ይገባል ብሏል። አስገዳጅ፣ በአገልግሎት ወይም በኮስት ሸሪንግ ለመክፈል ተፈራርመን ውል የገባንበት ሙያ ስለሆነ በግል ለመስራትና ሌላ ቦታ ለመሄድ ማናቆ አለብን ሲልም ገልጧል። መንግስት የገባውን ውል ሊያስፈፅም ይገባል ያለው ዶ/ር አቤኔዘር ክልሉ አልችልም ካለ በደብዳቤ ቢያሳውቀን የሚመለከተውን አካል ለመጠየቅ እንደሚመቻቸው ጠቁሟል። በጀት የተቋማት የአሰራር ጉዳይ ነው፣ እንደምክንያት እየተነሳ ለወራት መቀጠሉ ተገቢ አይደለም፣ ጉዳዩ የትኩረት ማነስ ነው ብሏል። ዶ/ር መልካሙ ተሰማ በበኩሉ አብዛኞች በ2012 አጋማሽ ዓመት የተመረቁ፣ ጥቂቶች ደግሞ 2013 መግቢያ አካባቢ የተመረቁ ጠቅላላ ሀኪሞች የችግሩ ሰለባ ስለመሆናቸው ገልጧል። የችግሩን አሳሳቢነት ሲያስረዳም ሌሎች ክልሎች ቋንቋንና ሌሎች በይፋም በህቡዕም የተለዩ መስፈርቶችን በማውጣት የእኔ የሚሉትን ሲቀጥሩ የአማራ ክልል ግን በኦፊሻል ማስታወቂያ ነው ሁሉን ነው የሚቀጥረው፣ በቅጥሩ ስራቸውን ለቀው ይወዳደሩበታል ብሏል። ግዴታችን እንወጣ፣ የመቀጠሪያ ደንቡ የፌደራል መንግስትን ባማከለ ይሁን፣ ክልሎች ሁሉ ወጥ የሆነ አሰራር ን ተከትለው ይቅጠሩ ሲል ነው ዶ/ር መልካሙ የጠየቀው። የደቡብ ክልል በጤና ጣቢያ የስራ ጫና እንዳለ ስለሚረዳ ሁለት እና ሶስት ጠቅላላ ሀኪሞችን በጤና ጣቢያ የሚመደብበት ተሞክሮ በአማራ ክልል እየተሰራበት አይደለም ብሏል። የጠቅላላ ሀኪሞች ላነሱት ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡን ያነጋገርናቸው አቶ መልካሙ አብቴ በክልሉ ጤና ቢሮ ም/ሀላፊ በአቶ ታሪኩ በላቸው በኩል ማብራሪያ እንዲሰጥ አድርገዋል። የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ታሪኩ በላቸው የዶክተሮች ቅሬታ አግባብ መሆኑን ገልፀው ችግሩን ለመፍታት ከሚመከለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል። ይሁን እንጅ ለቢሮው እየተመደበ ያለው በጀት የተመረቁ ሀኪሞችን በሙሉ ለመመደብ ለምናደርገው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ፈተና ሆኖብናል ብለዋል። በሌሎች ክልሎች ቋንቋን መሰረት ያደረገ የሀኪሞች ምደባም አግባብ አይደለም፤ አግባብ ያለው ቅጥር ወጥቶ ሁሉም መስፈርቱን የሚያሟላ ሁሉ እኩል የሚስተናገድበት አሰራርን እንዲከተሉ እየታገሉ ስለመሆናቸው የገለፁት አቶ ታሪኩ የተወሰኑ ያስተካከሉም አሉ ብለዋል። ከበጀት ጋር የተያያዘው ችግር ተፈቶ መፍትሄ የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲፈጠር እየሰራን እንገኛለን ነው ያሉት። የአማራ ሚዲያ ማዕከል ከዶክተሮች እና ከክልሉ ጤና ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ታሪኩ በላቸው ጋር ያደረግነውን ቆይታ በዩቱብ አድራሻው የሚያጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply