
“ለዘመናት የኖርንበትን ቤት ሲያፈርሱ ይሄ የእኛ ሀገር ነው፤ መጤ ናችሁ፤ ጠቅልላችሁ ወደ ሀገራችሁ ግቡ በማለት ነው” በለገጣፎ ድሬ ቀርሳ መድኃኒያለም ሰፈር ቤታቸው የፈረሰባቸው ነዋሪዎች አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … የካቲት 10 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ አበባ ዙሪያ ለገጣፎ ድሬ ቀርሳ መድኃኒያለም ሰፈር የሚኖሩ ነዋሪዎች ከየካቲት 8/2015 ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ቤታቸው እየፈረሰባቸው መሆኑን ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተናግረዋል። “ለዘመናት የኖርንበትን ቤት ሲያፈርሱ ይሄ የእኛ ሀገር ነው፤ መጤ ናችሁ፤ ጠቅልላችሁ ወደ ሀገራችሁ ግቡ በማለት ነው” ቤታችን በማፍረስ እያሳደዱን የሚገኙት ሲሉ ገልጸዋል። “ከዝርፊያ የተረፈ እቃችን እንኳ ይዘን ለመውጣት የማንችልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል” ሲሉም አማረዋል። የኦሮሙማ ኢፍትሃዊ አገዛዝን ሲገልጹም “ተመልሶ እንዳይመጣ እና እንዳይጠይቀን በሚል በራሴ ፍቃድ ለቅቄያለሁ በማለት እያስፈረሙ እያፈናቀሉን ይገኛሉ!” ብለዋል። እየደረሰብን ካለው አማራ ተኮር ጥቃት ሊታደገን የሚችል አካል አልተገኘም፤ በታጠቁ የኦሮሞ ታጣቂዎች እየታጀበ የሚመጣው አፍራሽ ግብረ ኃይልም የጭካኔውን ጥግ በመስራት ሁለንተናዊ እረፍት እየነሳን ይገኛል ሲሉ ገልጸዋል።
Source: Link to the Post