ለዘንድሮዉ ሐጅ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የመላዉ ዓለም ምዕመናን ሙስሊሞቹ ቅዱስት ከተማ በሚል ወደምትገለጸዋ መካ እየገቡ ነዉ ተብሏል ።የሳዑዲ አረቢያ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት እስከ ትናንት ድረ…

ለዘንድሮዉ ሐጅ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የመላዉ ዓለም ምዕመናን ሙስሊሞቹ ቅዱስት ከተማ በሚል ወደምትገለጸዋ መካ እየገቡ ነዉ ተብሏል ።

የሳዑዲ አረቢያ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት እስከ ትናንት ድረስ ከ1.5 ሚሊዮን የሚበልጡ የዉጪ ሐገር ዜጎች መካ ገብተዋል።

በመቶ ሺሕ የሚቆጠር የሳዑዲ አረቢያና እዚያዉ ሳዑዲ አረቢያ የሚኖር የሌሎች ሐገራት ምዕመንም ወደ መካ እየጎረፈ ነዉ።

እስከ ትናንት ድረስ መካ ከገቡት ምዕመናን መካከል 4ሺሕ 200ዉ እስራኤል በኃይል ከያዘችዉ ከፍልስጤም የምዕራባዊ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ የተጓዙ ናቸዉ።
እስራኤል በጋዛ ሠርጥ ላይ በከፈተችዉ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ ምክንያት ከጋዛ ሠርጥ ዘንድሮ ሐጂ የሚያደርግ የለም።

የሳዑዲ አረቢያ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ዘንድሮ ሐጂ የሚያደርገዉ ምዕመን ቁጥር ከአምናዉ በእጅጉ ይበልጣል።

አምና ሐጂ ያደረገዉ 1.8 ሚሊዮን ነበር።የዘንድሮዉ ሐጂ በይፋ የሚጀመረዉ ነገ አርብ ነዉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 06 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply