ለ“ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” ህዝበ ውሳኔ፤ ሶስት ሚሊዮን የሚጠጉ ድምጽ ሰጪዎች መመዝገባቸውን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

በሃሚድ አወል

“የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን” ለመመስረት በመጪው ጥር 29 ለሚደረገው ህዝበ ውሳኔ፤ 2.9 ሚሊዮን ድምጽ ሰጪዎች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። ለህዝበ ውሳኔው የተመዘገቡት ድምጽ ሰጪዎች ቁጥር፤ ቦርዱ በግምት ካስቀመጠው የመራጮች ብዛት በ200 ሺህ ገደማ ያነሰ ነው። 

ምርጫ ቦርድ በነባሩ የደቡብ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ለሚያካሄደው ህዝበ ውሳኔ ይመዘገባሉ ብሎ የገመታቸው ድምጽ ሰጪዎች ብዛት 3.1 ሚሊዮን ነበር። ብሔራዊው ምርጫ ቦርድ ለሁለት ሳምንት ገደማ ያህል ሲያካሄድ የቆየውን የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቁን በይፋ ያስታወቀው ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ታህሳስ 26፤ 2015 ነበር።

ቦርዱ አጠቃላይ የህዘበ ውሳኔውን ሂደት በተመለከተ ዛሬ ሰኞ በሰጠው መግለጫ፤ “ከፍተኛ የሆነ የህግ እና የአፈጻጸም ጥሰት” ተከስቶባቸዋል ባላቸው 24 የምርጫ ጣቢያዎች ድጋሚ ምርጫ እየተካሄደ እንደሆነ ገልጿል። መግለጫውን የሰጡት የቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ “እነዚህ ጣቢያዎች ላይ የነበሩትን የመራጮች ምዝገባ ሂደት እንዳለ ሰርዘን ድጋሚ የመራጮች ምዝገባ እንዲደረግ አድርገናል። ዛሬም እየተከናወነ ነው። በሚቀጥሉት ሁለት እና ሶስት ቀናት የመራጮች ምዝገባ፤ በእነዚህ 24 ጣቢያዎች ላይ እንደ አዲስ የሚከናወን ይሆናል” ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)  

[በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ ይታከልበታል]

The post ለ“ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” ህዝበ ውሳኔ፤ ሶስት ሚሊዮን የሚጠጉ ድምጽ ሰጪዎች መመዝገባቸውን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ appeared first on Ethiopia Insider.

Source: Link to the Post

Leave a Reply