ለዶ/ር አብይ የድጋፍ ሰልፍ እንዲካሄድ የተደረገ ኅብረተሰቡን በማስገደድ እንደሆነ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ አስታወቀ አሻራ ሚዲያ የካቲት 06/06/13/ዓ.ም ባህር ዳር ለዶ/ር አብይ የ…

ለዶ/ር አብይ የድጋፍ ሰልፍ እንዲካሄድ የተደረገ ኅብረተሰቡን በማስገደድ እንደሆነ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ አስታወቀ አሻራ ሚዲያ የካቲት 06/06/13/ዓ.ም ባህር ዳር ለዶ/ር አብይ የ…

ለዶ/ር አብይ የድጋፍ ሰልፍ እንዲካሄድ የተደረገ ኅብረተሰቡን በማስገደድ እንደሆነ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ አስታወቀ አሻራ ሚዲያ የካቲት 06/06/13/ዓ.ም ባህር ዳር ለዶ/ር አብይ የድጋፍ ሰልፍ እንዲካሄድ የተደረገ ኅብረተሰቡን በማስገደድ እንደሆነ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ አስታውቋል፡፡ የድጋፍ ሰልፍ አናደርግም ብለው ተቃውሟቸውን ያሰሙ ወጣቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ እንግልት እንደደረሰባቸው ፓርቲው አመላክቷል፡፡ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በኦሮሚያ ክልል ‹‹በሰላማዊ መንገድ የተቃውሞ ሠልፍ እያደረጉ ያሉ ዜጎችን የታጠቁ ኃይሎች በመሳሪያ አፈሙዝ እንዲታገቱ ተደርገዋል›› በሚል ድርጊቱን አውግዟል፡፡ በየካቲት ወር መጀመሪያ የብልጽግና ፓርቲ ኅብረተሰቡን በማስገደድ ለዶክተር ዐቢይ አሕመድ የድጋፍ ሠልፍ እንዲያካሄዱ መደረጉን ያስታወሰው ኦነግ፣ ይህ ሠልፍ በመንግሥት የታጠቁ ኃይሎች በመታጀብ በሰላም እንዲጠናቀቅ ተደርጓል ብሏል፡፡ ነገር ግን ለሠልፉ አሉታዊ መልስ የሰጡ ዕጣ ፋንታቸው መገደልና መደብደብ ሆኗል ሲል አመልክቷል፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በክልሉ እየተደረገ ነው ባለው የተቃውሞ ሠልፍ፣ በያቤሎ የካቲት 1፣ 2013 አንድ ሰው እንደተገደለ፣ እንዲሁም የካቲት 3፣ 2013 ሦስት ወጣቶች በድሬደዋ ከተማ በጥይት ተመተው ቆስለዋል ብሏል፡፡ ፓርቲው በአሁኑ ወቅት ሰላም እና መረጋጋት የተሳናትን ኦሮሚያን የላቀ ሰላም እንድታገኝ የኦሮሚያ ሽግግር መንግሥትን በማቋቋም ላይ ይገኛል ያለ ሲሆን፣ የኦሮሚያ ሽግግር መንግሥት ግንባታን በማጠናከር ሌሎች ጭቁን ኅብረ ብሔራዊያን ክልላቸውን በማረጋጋት የፈረሰውን መዋቅር መልሰው መገንባት ላይ አትኩረው እንዲሠሩ አሳስቧል ሲል አምባ ድጅታል ከትቦታል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply