ለጃዋር መሃመድ አራት ሲም ካርዶችን ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሊያቀብል ሲል ተይዟል የተባለው ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም…

ለጃዋር መሃመድ አራት ሲም ካርዶችን ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሊያቀብል ሲል ተይዟል የተባለው ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም…

ለጃዋር መሃመድ አራት ሲም ካርዶችን ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሊያቀብል ሲል ተይዟል የተባለው ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ተጠርጣሪው ግለሰብ ሃምዛ ጀማል መሃመድ ይባላል፡፡የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ተጠርጣሪው ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም. 1ኛው ሲም ካርድ በኦ ኤም ኤን ድርጅት ስም ማውጣቱን ጠቅሶ ሶስቱ ሲም ካርዶች ደግሞ በግለሰብ ስም የወጡ መሆናቸውን ከኢትዮ ቴሌኮም መጣራቱን ገልጿል፡፡ ግለሰቡ እነዚህን ሲም ካርዶች በመያዝ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት በመሄድ ጃዋር መሃመድን ልጠይቅ ነው በሚል ገብቶ ሲም ካርዶችን ለጃዋር መሃመድ ሊያቀብል ሲል መያዙንም አብራርቷል፡፡ ተጠርጣሪው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርቦ ጉዳዩ እየታየ ነው፡፡ ዘገባው የFBC ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply