You are currently viewing “ለገጣፎ ቀርሳ ድሬ የሚባል አካባቢ የተፈጸመ የግፍ ጥግ…..!”       በለጠ ካሳ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ …    የካቲት 17 ቀን 2015 ዓ/ም          አዲስ አበባ ሸዋ እየ…

“ለገጣፎ ቀርሳ ድሬ የሚባል አካባቢ የተፈጸመ የግፍ ጥግ…..!” በለጠ ካሳ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … የካቲት 17 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ እየ…

“ለገጣፎ ቀርሳ ድሬ የሚባል አካባቢ የተፈጸመ የግፍ ጥግ…..!” በለጠ ካሳ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … የካቲት 17 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ እየተጣደፉ ከመጡት አባት ጋር ቢሮ አካባቢ ተገናኘን። “ሁለት ልጆቿ በጅብ ተበሉባት” የሰቀቀን እንባ እየተናነቃቸው እንደገና ቀና ብለው “ባልተቤቷም ራሱን ሰቀለ ፤ ታንቆ ሞተ” “ለመሆኑ በአዲስ አበባ ዙሪያ ምን እንደሆነ የከተማው ሕዝብ ሰምቷል?! ሚዲያዎች ያውቃሉ?!” ለገጣፎ ቀርሳ ድሬ የሚባል አካባቢ የሆነውን አስቀድሜ ልንገርህ:- “…በውድቅት ሌሊት ቤቷን የሚያፈርሰው ግብረ ኃይል መጣ። ቤቱን በተኙበት ማፍረስ ጀመሩ። ሴትዮዋ ደንግጣ ወጣች። የሆነውን ማመን መቀበል አቅቷት እንደምንም ልጆቿን አወጣች። ልጆቹን ዛፍ ስር አስቀምጣ ተመልሳ የተወሰኑ ዕቃዎች ከዶዘር ጋር ተሻምቼ አፈር ሳይሆኑ ላውጣ ብላ ሄደች። ስትመለስ ከዛፍ ሥር ከተቀመጡት ህፃናት አንዱ በጅብ ተወስዷል። አንዱ በጅብ ተነክሶ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል። አክለውም አሁን በከፋተኛ ሁኔታ በጅብ የተነከሰው ሕፃን ምናልባት ሳይሞት አይቀርም ይላሉ።” እኔም ጎረቤት ነበርሁ ሃዘን አልደረስሁም። ራሷን እንዳታጠፋ ሴትዮዋ በገመድ ታስራ ነው ያለችው። እናቲቱ።” “ሌላው አሰቃቂ መረጃ በተለምዶ 44 ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ነው የሆነው። ቤት አናስፈርስም የሚሉ በርካታ ሰዎች በጥይት ተገድለዋል። እኔ ስምንት ሰዎች መሞታቸውን አውቃለሁ። በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን ሐኪም ቤት ተገኝቼ በዓይኔ አይቻለሁ። ከተገደሉት ስምንት ሰዎች አንዷ ድርስ ነፍሰጡር ነች። በጥይት ነው የተገደለችው። የእሷ ባልተቤት ነው ራሱን ሰቅሎ። ታንቆ የሞተው።” በአዲስአበባ ከተማ ዙሪያ በመንግሥት እየተፈፀመ ካለው መጠነ ሰፊ የቤት ማፍረስ መረሃ ግብር ጋር በተያያዘ ለጆሮ የሚሰቀጥጥ ግፍ እየተሰማ ነው። እባካችሁ ለሕዝብ አድርሱልን። እባካችሁ ምን እስክንሆን ነው የሚጠበቀው?! ሌላ ሚዲያ ካለ ድምፄን ላሰማ እስኪ ብለው እንባቸውን እየጠራረጉ ሄዱ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply