
ለጉብኝት ከከተማ በወጡ ሕጻናት ላይ የትራፊክ አደጋ ደረሰ 👉በአደጋው እስካሁን የ4 ሕጻናት ተማሪዎችና የአንድ መምህርት ሕይወት አልፏል =======#======= መጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ከእንጅባራ ከተማ የመዋለ ህጻናት ተማሪዎችን ይዞ ለጉብኝት የወጣ መኪና ባጋጠመው የትራፊክ አደጋ የ4 ሕጻናት ተማሪዎችና የአንድ መምህር ሕይወት ማለፉ ተስምቷል፡፡ የእንጅባራ ኮሙኒኬሽን የትራፊክ አደጋው መድረሱን የሚያረጋግጥ መረጃ በገጹ የለጠፈ ቢሆንም፣ ዝርዝር መረጃ አላወጣም፡፡ አዲስ ማለዳ ስለትራፊክ አደጋው ባደረገችው ማጣራት አደጋው ያጋጠመው “ዳሳሽ አካዳሚ” የተባለ የሕጻናት ትምህርት ቤት ሕጻናት ተማሪዎች ላይ ነው፡፡ ሕጻናቱ በሰርቪስ መኪና “ዶንደር ፏፏቴ” ወደ ተባለ ቦታ ዛሬ መጋቢት 22/2015 ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ለጉብኝት ከከተማ ወጥተው እንደነበር ተሰምቷል፡፡ የትራፊክ አደጋው ከባድ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፣ እስካሁንም የ3 የሕጻናት ሕይወት ወዲያውኑ ማለፋና፤ አንድ ሕጻንና እና አንዲት መምህርት ወደ ሕክምና እንደደረሱ ሕይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል። ከባድ የአካል ጉዳት ያጋጠማቸው ህጻናት መኖራቸውም የተጠቆመ ሲሆን፤ የአካል ጉዳት ያጋጠማቸው ህጻናት በእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል ሕክምና እያገኙ መሆኑ አዲስ ማለዳ ከአካባቢው ያገኘችው መረጃ ያመላክታል፡፡ ወደ ሕክምና ከገቡት መካከልም 4ቱ አገግመው ወደ ቤተሰቦቻቸው መቀላቀላቸው ተነግሯል። © አዲስ ማለዳ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post