ለግንዛቤ ያህልበእድሜ የገፉ ሰዎች እና የወር አበባ ማየት ያቆሙ ሴቶች ይበልጥ ተጋላጭ የሚሆኑበት የአጥት መሳሳት የጤና እክልህመሙ ሊታያውቅ የሚችለው ታካሚዎች ስብራት ሲያጋጥማቸው ወደ ጤና…

ለግንዛቤ ያህል

በእድሜ የገፉ ሰዎች እና የወር አበባ ማየት ያቆሙ ሴቶች ይበልጥ ተጋላጭ የሚሆኑበት የአጥት መሳሳት የጤና እክል

ህመሙ ሊታያውቅ የሚችለው ታካሚዎች ስብራት ሲያጋጥማቸው ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ በሚደረግላቸው ምርመራ ላይ ሊሆን እንደሚችል ሰምተናል፡፡

አጥንት በቀላሉ ለጉዳት ተጋላጭ ባይሆንም በአጥንት ላይ የመሳሳት ሁኔታ ካጋጠመ ግን ጉዳቱን ለመጠገን አስቸጋሪ ያደርገዋል ተብሏል፡፡

የአጥንት መሳሳት የምንለው አጥንት ጥንካሬውን ሲያጣ ነው፤ በዚህም ምክንያት የአጥንት መድከም እንዲያጋጥም ምክንያት እንደሚሆን ተመላክቷል፡፡

ዶክተር ቃልአብ ተስፋዬ የአጥንት እና የስብራት ስቴሻሊስ ናቸው፡፡
የአጥንት መጠን መቀነስ የአጥንት መሳሳት የሚያስከትል ሲሆን፤ ሴቶች የወር አበባ ማየት ካቆሙ በኋላ እና ከ70 ዓመት በላይ የሆኑ ወንዶች ለአጥንት መሳሳት ተጋለጭነታው ሊጨምር ይችላል ብለዋል፡፡ ለአጥት መጎልበት የሚረዱ ሆርሞኖች ካቆሙ በኋላ በሴቶች ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡

ያተለመደው የአጥንት መጠን በወጣቶች ላይ የሚከሰት ሲሆን: ይህም አልኮል መጠጥ የሚያዘወትሩ እና የሚያጨሱ ሰዎች ተጋላጭ ይሆናሉ ተብሏል፡፡
መነሻ ምክንያት፤
• በእድሜ በገፉ ሰዎች እና የወር አበባ ማየት ያቆሙ ሴቶች
• ከዚህ በፊት የአጥንት ስብራት በተደጋጋሚ የገጠማቸው
• የስቴሮይድ መድሃኒት አይነቶችን የሚጠቀሙ ሰዎች
• የዘር ፍሬ በኦፕሬሽን ማስወጣት
• ተጓዳኝ የጤና እክል ያለባቸው ሰዎች እንደ ተጋላጭነታቸው ሊጨምር ይችላል ተብሏል፡፡

የሚስተዋሉ ምልክቶች
የአጥንት መሳሳት ምንም አይነት ምልክት በታማሚው ላይ ላይስተዋል ስለሚችል ህመሙ የከፋ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ምክንያት የሚሆንበት ሁኔታ መኖሩ ተናግረዋል፡፡

ለህመሙ ምልክቶች ይህ ነው ለማለት አስቸጋሪ ቢሆንም፤
• የዳሌ እና ወገብ አከባቢ ለስብራት ተጋላጭ ባይሆንም የአጥንት መሳሳት ካለ ለስብራት ሊያጋጥም ይችላል፡፡
• ከህመሙ ጋር በተያያዘ በወገብ፣አከርካሪ ላይ፣ በመዳፍ እና በሰዓት ማሰሪያ አንጓ ላይ ስብራቶች ሊስተዋሉ ይችልሉ ፡፡
• የአጥንት መሳሳት ያጋጠማአቸው ሰዎች አጥንታቸው በቀላሉ ሊሰበር እና ስብራት ለመጠገን አስቸጋሪ ያደርጋል ተብሏል፡፡
• የድካም ስሜት ሙሉ ሰውነት መቆረጣጠም እና የወገብ ህመም ነእንደሚስተዋሉ ታማሚዎች ሲናገሩ ይደበጣል ብለዋለል፡፡

ህክምናው ፤
ህክምናው እንደ አጥንት መሳሳት ደረጃ የሚወሰን ነው ተብሏል፡፡
በአጥንት መሳሳት ምክንያት የሚፈጠር የአጥንት ስብራት በአብዛኛው የሚፈጠረው በዳሌ አካባቢ፤በአከርካሪ አጥንት ላይ እና የሰዓት ማሰሪያ አንጓ ላይ በመሆኑ፤ በእነዚህ የሰውነት ክፍሎት ላይ DEXA የሚባል መሳሪያን በመጠቀም ታካሚዎች የአጥንት መጠን የሚለካ ይሆናል ሲሉ ባለሞያው ተናግረዋል፡፡

ከምርመራው በኋላ
• የአጥንት መሳሳትን የሚመልሱ መድሃኒቶችን እና ካልሲየም፣ የቫይታሚን ዲ ለታካዎች የሚታዘዝላቸው ይሆናል
• ከአጥንት መሳሳት ጋር ተያይዞ የአጥንት ስብራት ካጋጠመ የአጥንት ስብራቱን የቀዶ ጥገና ህክምና እንደሚሰጥ ተጠቁሟል፡፡

ህመሙን ቀድሞ ለመከላከል፤
የአጥንት መሳሳት ምንም አይነት የህመም ምልክቶችን ሳያሳይ ለእረጅም ጊዜ ሊቆይ እንደሚችል ባለሞያው ከጣያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ነግረውናል፡፡

እድሜን ተከትሎ የአጥንት መሳሳት ችግር በብዛት ሴቶች ላይ ቢከሰትም ወንዶችም ቢሆኑ ለህመሙ ተጋላጭ የሚሆኑበት ሁኔታ መኖሩን ተነግሯል፡፡
በዳሌ አጥንት ላይ የሚደርስ ስብራት አልያም መሰንጠቅ ከባድና ለከፋ ጉዳት የሚዳርግ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በመሆኑም የአጥንት ጥንካሪ ከ20 ዎቹ እድሜ በኋላ እየቀነሰ እንደሚሄድ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

በየእለቱ መደበኛ የሰውነት እንቅስቃሴን ማዘውተር፣ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣ ለከፍተኛ የጸሃይ ብርሃን ተጋላጭነትን መቀነስ ፣ እንዲሁም ካልሲየም እና ቫይታሚን ዲ ማግኘት ህመሙን ቀድሞ ለመከላል ይረዳል ተብሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የእግር ጉዞን ማድረግ ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

እሌኒ ግዛቸው

መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply