ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተነሱ አበይት ጥያቄዎች መካከል

ማክሰኞ ኀዳር 6 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በዛሬው የሕ/ተ/ ምክር ቤት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተነሱ አበይት ጥያቄዎች መካከል

👉የሰላም ስምምነት እና ጦርነቱን በሚመለከት
1. የሰላም ስምምነቱን ጥቅምና ጉዳቱ እንዲብራራ፣ አተገባበሩን በሚመለከትም ጠ/ሚኒስትሩ ማብራርያ እንዲሰጡ ተጠይቋል፡፡

2. የትግራይ ክልልን እና ጦርነት የተካሔደባቸውን አካባቢዎች መልሶ ግንባታ ሥራ በፍጥነት እና በፍትሐዊነት ሁሉንም አካባቢዎች ያዳረሰ ሥራ እንዲሠራ መንግሥት ያለው ቁርጠኝነት እንዲብራራ

3. ስምምነቱን የብልጽግና መንግሥት ብቻውን የመደራደሩ ተገቢነትና እየተነሱበት ባሉ የተቃውሞ ድምጾች ዙርያ ማብራርያ እንዲሰጥ

4. በስምምነቱ “በሕገ መንግሥቱ መሠረት ይፈታሉ” የተባሉት ጥያቄ ያለባቸው አካባቢዎች ችግር የተፈጠረው ከሕገ መንግሥቱ በፊት በመሆኑ፣ አካባቢዎቹ ታግለው ነፃነት ካገኙ በኋላ ይህ መወሰኑ መብታቸውን የሚጋፋ ነው

👉ከሰሜኑ ጦርነት በመለስ
1. ዜጎች ከቦታ ቦታ በነፃነት የመንቀሳቀስ መብታቸው እየተከበረ አይደለም፤ በተለይ ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ዜጎች ለከፍተኛ ችግር እየተጋለጡ መሆናቸውን በሚመለከት

2. በየ አካባቢው በገመድ ኬላ እየተሠራ ሕዝቡን የኮቴ ክፈሉ የሚሉ “ጉልበተኛ ነን የሚሉ” ተብለው የተገለጹ አከላትን በሚመለከት

3. በጥቅሉ በሕገ መንግሥቱ መሠረት የዜጎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ የመሥራትና ሀብት የማፍራት መብት የሚከበረው መቼ ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡

4. የክልል ልዩ ኃይልን በአንድ መከላከያ እዝ ስር ለማዋል ምን እየተሠራ ነው?

5. የመንግሥት አገልግሎቶች ያለ እጅ መንሻና መማለጃ የማይገኙ እየሆነ ዜጎች መብታቸውን ለመጠቀም ገንዘብ ለመክፈል እየተገደዱ ስለመሆናቸውና ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል የተባለውን ሙስና ለመግታት ምንግሥት ምን እየሠራ ነው?

6. የምክር ቤት አባላት የወከላቸውን ሕዝብ መሠረተ ልማቶች እንዳይጎበኙ ስለመከልከላቸው

7. መንግሥትን እና አሠራሩን የሚተቹ ጋዜጠኞች እና ግለሰቦች እየታፈኑና አላግባብ እየታሠሩ ስለመሆናቸው

👉የሕግ የበላይነት በኦሮሚያ ክልል አደጋ ውስጥ መግባቱን በሚመለከት
1. የሕግ የበላይነትን የማስከበር ጉዳይ በተለይ በኦሮሚያ በኦነግ ሸኔ በርካታ አካባቢዎች በሥሩ ሆነው ሕዝብና የፀጥታ አስከባሪዎች ለጉዳት እየተዳረጉ መሆናቸው

2. መንግሥት ኦነግ ሸኔን ለመቆጣጠር የተከተለው አቅጣጫ ትክክል ነው ብለው ያምናሉ? ወለጋ ከኦነግ ሸኔ ነፃ መውጣት አልቻለችም

3. የኦነግ ሸኔን ጉዳይ ለመፍታት መንግሥት ኃይልን ብቻ ይጠቀማል ወይስ የሰሜኑን ጦርነት የፈታበትን መንገድ ይከተላል?

4. ኦነግ ሸኔ የትጥቅ ምንጩስ ምንድነው?

ምጣኔ ሀብት እና የኑሮ ውድነትን በሚመለከት

1. የመሠረታዊ ሸቀጦች አቅርቦት መጥፋትና ዋጋ መናር፤ የግብይት ሰንሰለቱ በአሻጥር የተሞላ መሆን፣ የወጣቶች የሥራ አጥነት ችግር፣ የምግሥት ሠራተኞች እና የጡረተኞች ገቢ ኑሮን መቋቋም የሚያስችል አለመሆኑ፣ ሕብረተሰቡን የሚፈታተኑ በመሆኑ ከአጭርና ረዥም ጊዜ መፍትሔ አንፃር መንግሥትዎ ምን እየሠራ ነው?

2. ኢንቨስትመንትን በሚመለከት ቢሮክራሲና ብልሹ አሠራሮች የዘርፉን ባለሀብቶች እየገፋ በመሆኑ መንግሥት ዘርፉን እንዲያስተካክል

እንዲሁም የድሬደዋ ከተማ እና የአዲስ አበባ ከተማን በሚመለከት ከመልካም አስተዳደር እስከ ከፍተኛ መዋቅራዊ ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡

The post ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተነሱ አበይት ጥያቄዎች መካከል first appeared on Addis Maleda.

Source: Link to the Post

Leave a Reply