ለጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ገቢ የተደረገው ደብዳቤ!ከ300 በላይ የኮቪድ 19 ጤና ባለሞያዎች ከስራ ገበታቸው በመባረራቸው ለጠ/ሚ ጽህፈት ቤት የቅሬታ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተነገረ።የጤና ሚኒስ…

ለጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ገቢ የተደረገው ደብዳቤ!

ከ300 በላይ የኮቪድ 19 ጤና ባለሞያዎች ከስራ ገበታቸው በመባረራቸው ለጠ/ሚ ጽህፈት ቤት የቅሬታ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተነገረ።

የጤና ሚኒስቴር ከሶስት አመት የኮንትራት ውል በኋላ 340 የሚሆን የኮቪድ 19 የጤና ባለሞያዎች ከስራቸው አሰናብቷል ተብሏል፡፡

በዚህም ምክንያት ከስራ ገበታቸው የተሰናበቱት የጤና ባለሞያዎቹ ለጠ/ሚ ጽህፈት ቤት የአቤቱታ ደብዳቤ መላካቸው ተገልጿል፡፡

ባለሙያዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በላኩት ደብዳቤ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በኮንትራት እንደቀጠራቸው አንስተዋል፡፡

ነገር ግን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ውላቸውን ዘላቂ የሚያደርግ መመሪያ ቢያወጣም የጤና ሚንስቴሩ ግን ከስራቸው እንዳገዳቸው ገልጸዋል፡፡

ከመጋቢት 2010 ዓ.ም ጀምሮ በኮንትራት ሲያገለግሉ የቆዩት የጤና ባለሙያዎች የወጣውን የቋሚ ቅጥር መመሪያ በመጣስ ከስራ በመባረራቸው ነው ለጠ/ሚ ጽህፈት ቤት ቅሬታ ያቀረቡት፡፡

ቅሬታ አቅራቢዎቹ ቋሚ የተደረጉም እንዳሉ በመግለጽ እኛ ተለይተን የምንሰናበትበት ምንም ምክንያት የለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ስማቸው እንዳይገለጽ ከጠየቁ ቅሬታ አቅራቢዎች መካከል አንዱ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገረው፣በደብዳቤ በቋሚነት እንደሚቀጠሩ ቢነገራቸውም ዕድሉን ያገኙት 80 በመቶዎቹ ብቻ ናቸው።

የጤና ባለሙያዎቹ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ከጤና ሚኒስቴር ምንም አይነት መፍትሄ ማግኘት ባለመቻላቸው ለጠ/ሚ ሚኒስቴር ጸህፈት ቤት ቅሬታ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ በበኩላቸው ሲቪል ሰርቪሱ የጤና ባለሙያዎቹ በሚሰሩበት የጤና ተቋም አቅም መሰረት ቋሚ እንዲሆኑ መፍቀዱን ተከትሎ ከ5 ሺህ በላይ የጤና ባለሞያዎች ቋሚ እንዲሆኑ ተደርጓል ብለዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው እንደተናገሩት “ተቋማቱ በስራ አፈጻጸማቸው ጉድለት ላገኘባቸው እና የስነ-ምግባር ችግር ታይቶባቸዋል ላላቸው ባለሙያዎች ቋሚ ኮንትራት አለማቅረቡን አንስተዋል።

በመሆኑም የጤና ባለሙያዎቹን ውል በማቋረጥ ላይ ምንም አይነት የመብት ጥሰት የለም፤ ነገር ግን ባለሙያዎቹ የጤና ተቋማቱ ስህተት ሰርተዋል ብለው የሚያስቡ ከሆነ በህጋዊ መንገድ መጠየቅ ይችላሉ ብለዋል።

በመሳይ ገ/መድህን

ታህሳስ 19 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply