ለጠ/ሚ ዐቢይ በተጠራ ሰልፍ ላይ ቦንብ በመወርወር የሰው ህይወት በማጥፋትና የአካል ጉዳት በማድረስ ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች ላይ ከ5 እስከ እድሜ ፅኑ እስራት ተበየነባቸው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተጠራው የድጋፍ ሰልፍ ላይ በመስቀል አደባይይ በቦንብ በመወርወር የሁለት ሰዎች ህይወት እንዲያልፍ እና በ150 ሰዎች የአካል ጉዳት መድረስ ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ 5 ግለሰቦች ከ5 ዓመት እስከ እድሜ ልክ ፅኑ እስራት ቅጣት ተወሰነባቸው ።
 
ቅጣቱ የተወሰነው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የህገ መንግስት እና የፀረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
 
በዚህም ሶስተኛ ተከሳሽ አቶ ጥላሁን ጌታቸው በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት የተቀጣ ሲሆን ቀሪዎቹ ከአምስት ዓመት እስከ 23 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።
 
በታሪክ አዱኛ

The post ለጠ/ሚ ዐቢይ በተጠራ ሰልፍ ላይ ቦንብ በመወርወር የሰው ህይወት በማጥፋትና የአካል ጉዳት በማድረስ ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች ላይ ከ5 እስከ እድሜ ፅኑ እስራት ተበየነባቸው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply