ለጤና ባለሙያዎች የምስጋና ፕሮግራም ሊዘጋጅ ነዉ፡፡ሀገር በኮሮና ቫይረስ ችግር ዉስጥ በገባችበት ጊዜ ከፊት ሆነዉ አገልግሎት ሲሰጡ ለነበሩ የህክምና ባለሙያዎች የእዉቅና እና የምስጋና ፕሮግራ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/NRSAV3iOxAjsndeznAkh8BX86rW5Ksvdyj5Koo-RcYYCWBqrv8BWuVaHSZjEDlzionRolFFAdpKCo2Ng9V6exonAAyynU6vZgfRLQDGRm2fybOaxyYwQ77-RYvLEyny6sKWKJ3Nu4pTeG3NxQI_XCCUNkOeDapjD7t9gr9bXjWvLU3iuCT4lXWIVE-HSMWdTj1ZHwFuqiuq_hjWLm75TbbNI4cS9xGgw4DRn3QN_QQ5FgikbTrCc3U2X2lpBWkC0GUj_h7kXGb3G8Pk94PDieQnOftTvK-ZdbvimdPKM62xor4x8kw_6IVJ8nHOGrtzMgF_C1xP-AX_0J6ZpFQLbKg.jpg

ለጤና ባለሙያዎች የምስጋና ፕሮግራም ሊዘጋጅ ነዉ፡፡

ሀገር በኮሮና ቫይረስ ችግር ዉስጥ በገባችበት ጊዜ ከፊት ሆነዉ አገልግሎት ሲሰጡ ለነበሩ የህክምና ባለሙያዎች የእዉቅና እና የምስጋና ፕሮግራም ሊዘጋጅ ነዉ፡፡
ፕሮግራሙ የፊታችን ጥቅምት 12 በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል እንደሚካሄድ የገለጸዉ ዳንኪራጃም ኘሮሞሽን እና ኘሮዳክሽን ሲሆን በዕለቱም የጤና ባለሙያዎች ለሰሩት ስራ ይመሰገናሉ ተብሏል፡፡

የዳንኪራጃም ኘሮሞሽን እና ኘሮዳክሽን ኘሮግራም ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ እንደገለጹት፣ የህክምና ባለሙያዎች የኮቪድ 19 በሽታ እንዳይስፋፋ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በመስራት፣ የበሽታው ምልክት የታየባቸውን በመመርመር እንዲሁም ህሙማንን በመንከባከብ የራሳቸውን ህይወት አደጋ ውስጥ በመክተት ጭምር የህክምና አገልግሎት ሲሰጡ ለነበሩ ተቋማት እና ባለሙያዎች እውቅና እና የምስጋና ኘሮግራም ተዘጋጅቷል ነዉ ያሉት፡፡

በዕለቱ ከሚኖረዉ የምስጋና እና የዕዉቅና ፕሮግራም ባሻገር የመዝናኛ ዝግጅቶች እና የምክክር እንዲሁም የውይይት ኘሮግራም እንደተሰናዳም ገልጸዋል፡፡
የኮሮና ቫይረስ በዓለምም በሃገራችንም ያስከተለዉ ቀዉስ የበርካታ ድርጅቶችን ኢንቨስትመንት አቃውሷል እንዲሁም የሀገራችን ኢኮኖሚ ላይም አሉታዊ ተጽዕኖ አሳርፏል፡፡

ዳንኪራጃም ፕሮዳክሽን እና ፕሮሞሽን የኢትዮጵያን ባህል በተለይም የሙዚቃውን ኢንዱስትሪ በመላው ዓለም ለማስተዋወቅ ለኢትዮጵያዊያን የሙዚቃ ባለሙያዎች ድጋፍ በማድረግ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ለምዕራቡ ዓለም እና በውጭ ላሉ ኢትዮጵያውያን በስፋት ሲያስተዋውቅ መቆየቱ በመግለጫዉ ላይ ተነስቷል፡፡

በእስከዳር ግርማ
መስከረም 25 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply