ለጤና ተቋማት እና ለሆስፒታሎች ከቀረበ የዱቤ ሽያጭ የህክምና ግብዓቶች 2 ቢሊዮን ብር አልተከፈለም ተባለ

8 ቢሊየን ብር የሚያወጣ የህክምና ግብዓቶችን ለጤና ተቋማት እና ለሆስፒታሎች ማቅረቡን የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት አስታውቋል።

በተያዘው በጀት ዓመት በ6 ወራት ውስጥ 6 ቢሊየን ብር የሚሆነው የዱቤ የመድሃኒት ሽያጭ መሆኑን የተናገሩት የአገልግሎት የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አወል ሀሰን፤ የ2 ቢሊዮን ብር ብቻ የእጅ በእጅ የህክምና ግብዓት ሽያጭ መከናወኑን ተናግረዋል።

የጤና ተቋማት እና ሆስፒታሎች የበጀት እጥረት ሊያጋጥማቸው የሚችል ቢሆንም የመድሃኒት ግብዓቶችን ለጤና ተቋማት በዱቤ ሽያጭ ካቀረቡ በኋላ የማይመለስበት ሁኔታ አስቸጋሪ ሆኗል ብለዋል።

በመላ ሀገሪቱ በ19 ቅርንጫፍ ስር በሚገኙ 5 ሺህ የመንግስት የጤና ተቋማት ከ8 መቶ 40 በላይ የሚሆኑ ሆስፒታሎች ሲሆኑ በወር እና በየ2 ወሩ የመድሃኒት ግብዓት ግዢ እንደሚያከናውኑ ተጠቁሟል።

የመድሃኒት የዱቤ ሽያጭ ገንዘብ በወቅቱ አለመመለሱን ተከትሎ አገልግሎቱ በፋይናንስ እራሱን እንዳይችል እና በተቋሙ ላይ የገንዘብ እጥረት እንዲከስት፣ የገንዘብ የመድሃኒት የመግዛት አቅም እንዲቀንስ እንዲሁም መድሃኒት ለመግዛት እንዲቸገሩ መዳረጋቸውን ገልጸዋል።

በመሆኑም ለጤና ተቋማት እና ሆስፒታሎች ውል በተገባለት አቅረቦት መሰረት መድሃኒቶች እና የመድሃኒት ግብዓቶች የሚሰራጭ ይሆናል ተብሏል፡፡

የጤና ተቋማት ብድሮችን ቃል በገቡት ቀን የማይከፍሉ ከሆነ እና የኢትዮጲያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎትም መድሃቶችን በወቅቱ የማያቀርቡ ከሆነ በውሉ ተጠያቂ የሚሆኑበት ሁኔታ እንዲኖር መደረጉ ተገልጿል፡፡ ከዚህ በኋላ ውል በተገባለት አቅረቦት መሰረት መድሃኒቶች የሚሰራጭ ይሆናል ብለዋል።

የዱቤ ሸያጭ መስጠት የስልጣኔ መግለጫ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ የመድኃኒት ግብዓት የዱቤ ሽያጭ ገንዘብ ሳይከፈሉ እስከ 5 አመት የሚቆዩበት ሁኔታ በመኖሩ ለአገልግሎቱ አስቸጋሪ ሆኗል ተብሏል። ለጤና ተቋማት የሚሰጡ ነፃ የመድኃኒት ግብዓቶች በዱቤ ሽያጭ ውስጥ እንደማይካተት ተመልክቷል።

እሌኒ ግዛቸው
ሚያዝያ 01 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply