ለጸጥታው ምክር ቤት የቀረበው ገለጻ “በእውነታ ላይ ያልተመሰረተ ነው” – አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ

የጸጥታው ምክር ቤት (UNSC) ትናንት የኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ባደረጉት በዝግ ስብሰባ “ገለጻው የመንግስትንና የሌሎች ሰብዓዊ አጋሮችን ጥረት ዝቅ ያደረገ እና የሚያደናቅፍ” መሆኑን አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታዎች ማስተባባሪያ ተቋም (OCHA) ትናንት ለተሰበሰበው የድርጅቱ የጸጥታው ምክር ቤት (UNSC) ሰጥቷል ባለችው “በእውነታ ላይ ያልተመሰረተ ገለጻ” መስጋቷን ገለጸች፡፡

ገለጻውን በማስመልክት በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተቋሙ (OCHA) ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጋዳ ኤል ጣሂር ጋር መወያየታቸውን አል ዐይን ገልጸዋል፡፡

ተቋሙ ለምክር ቤቱ “በሰጠው ጠቃሚ ያልሆነ ገለጻ መስጋታችንን ገልጸናል”ያሉት አምባሳደር ታዬ “ገለጻው የመንግስትንና የሌሎች ሰብዓዊ አጋሮችን ጥረት ዝቅ ያደረገ እና የሚያደናቅፍ” መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

“ችግሮችን ለመሻገር የሚያስችልና በእውነታ ላይ የተመሰረተ አካሄድ አስፈላጊነት ላይ” ከምክትል ዋና ዳይሬክተሯ ጋር በአጽንኦት መወያየታቸውንም ነው አምባሳደር ታዬ በይፋዊ የማህበራዊ ገጻቸው ያሰፈሩት፡፡

ማርክ ሎውኩክ የተባሉት የOCHA ዋና ዳይሬክተር ትናንት ለምክር ቤቱ ገለጻ ባደረጉበት ወቅት በትግራይ ክልል ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ “ይበልጥ እየተባባሰ” መምጣቱን እና ጾታዊ ጥቃቶች “አሁንም በጦርነቱ መሳሪያ ሆነው እያገለገሉ” እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

በተገባው ቃል መሰረት የኤርትራ ወታደሮች ከክልሉ እየወጡ አይደለም” ሲሉ ማብራራታቸውንም ነው እንደነ ኤኤፍፒ ዓይነት ዓለም አቀፍ ብዙሃን መገናኛዎች የዋና ዳይሬክተሩን ንግግር ዋቢ አድርገው የዘገቡት፡፡

ይህን “ይበልጥ እየከፋና እየተባባሰ የመጣ የሰብዓዊ ቀውስ ሁኔታ ከተኩስ አቁም ውጭ ለማስቆም እንደማይቻል” ስለመናገራቸውም ተዘግቧል፡፡

“በግጭቱ የተፈናቀሉ 4 ሰዎች በርሃብ ሞተዋል” እንዲሁም ማክሰኞ ዕለት በርሃብ 150 ሰዎች መሞታቸው የሚያሳይ ሪፖርት በዚህ ሳምንት መቀበላቸውንም ሎውኩክ ገልጸዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ጸ/ቤት ኃላፊ ገብረመስቀል ካሳ  ለትግራይ ቴሌቭዥን በሰጡት መግለጫ  አሁንም ድረስ በክልሉ በርሃብ የሞቱ ሰዎች እንዳሉ  መስማታቸዉን የገለፁ ሲሆን የጽ/ቤታቸዉ ቀዳሚ ትኩረት እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡

የጊዚያዊ አስተዳደር ጸ/ቤት ኃላፊ እንዳሉት ከሆነ ቢያንስ በክልሉ 4.5 ሚልዮን ህዝብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ተደራሽ እንዳልሆነ እና በሁለተኛ ዙር እርዳታ ክፍፍል ለ2.5 ሚሊዮን ህዝብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 08 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

Source: Link to the Post

Leave a Reply