ለፈተና ሀዋሳ ዩኒቭርሲቲ በገቡ የ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ ድልድይ ተደርምሶ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ፡፡ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ዛሬ ጠዋት በሀዋሳ ዩኒቨርስ…

ለፈተና ሀዋሳ ዩኒቭርሲቲ በገቡ የ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ ድልድይ ተደርምሶ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ፡፡ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ዛሬ ጠዋት በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዉን ኹለት ካምፓሶች የሚያገናኝ ድልድይ በመፍረሱ ምክንያት ድልድዩን ሲሻገሩ በነበሩ የተወሰኑ ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸዉ እንደሚገኝም ተነግሯል። ሚኒስቴሩ የተማሪዎቹን ኹኔታ መላዉ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ እና የትምህርት ሚኒስቴር ግብረሀይል በቅርበት እየተከታተለ እንደሚገኝ የገለጸ ሲሆን፤ ወላጆች እንዳይደናገጡም ጠይቋል፡፡ ጉዳት የደረሰባቸዉ ተማሪዎች በቀጣይ በሚሰጠዉ ፈተና የሚፈተኑ መሆኑን የገለጸው የትምህርት ሚኒስቴር፤ ሌሎች ተማሪዎች በአጋጣሚዉ ሳይረበሹ ተረጋግተዉ እንዲፈተኑ አሳስቧል፡፡ ኹኔታዉን በሚመለከት ዝርዝር መረጃዎችን በቀጣይ እንደሚያሳውቅም የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply