ለፈተና ተብሎ ኢንተርኔት የማቋረጥ እቅድ እንደሌለ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ገለጹ አሻራ ሚዲያ የካቲት 29/06/ 2013 ዓ.ም ባህር ዳር  በ12ኛ ክፍል ተማሪዎ…

ለፈተና ተብሎ ኢንተርኔት የማቋረጥ እቅድ እንደሌለ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ገለጹ አሻራ ሚዲያ የካቲት 29/06/ 2013 ዓ.ም ባህር ዳር በ12ኛ ክፍል ተማሪዎ…

ለፈተና ተብሎ ኢንተርኔት የማቋረጥ እቅድ እንደሌለ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ገለጹ አሻራ ሚዲያ የካቲት 29/06/ 2013 ዓ.ም ባህር ዳር በ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና ሰበብ ኢንተርኔት እንደማይቋረጥ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው መስማቱን ኢትዮጵያ ቼክ የተባለው ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ለሚካሄደው ፈተና የሀገር ውስጥ እና የውጭ ተንታኞች፣ ጸሐፊዎች እና የማኅበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች የፈተና መሰረቅን ለመከላከል ከዚህ ቀደም እንደተደረገው ሁሉ ከዛሬ ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ ኢንተርኔት እንደሚቋረጥ እየፃፉ እንደሚገኙ ያመለከተው ድረ ገጹ፣ አንዳንድ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም ለሠራተኞቻቸው ይህን በኢሜይል ማሳወቃቸውን ገልጧል፡፡ … ሆኖም ዋና ዳይሬክተሩ ‹‹ፈተና ለመስጠት የግድ ኢንተርኔት መዘጋት አለበት የሚል አሠራር እንዳለ ተደርጎ መታሰቡ ከየት የመጣ እንደሆነ ግልፅ አይደለም፣ ፈተና ለመስጠት ሲባል ኢንተርኔት ለመዝጋት የተያዘ እቅድ የለም፣ ኢንተርኔት እየዘጉ ፈተና የመስጫ ግዜ ድሮ አልፏል›› ማለታቸውን አስነብቧል፡፡ በጉዳዩ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌም ኢንተርኔት የመዝጋት እቅድ እንዳለ እስካሁን አላውቅም ያሉ ሲሆን፣ የኢትዮ ቴሌኮም የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በበኩሉ በዚህ ዙርያ የደረረሰው መረጃ እንደሌለ ማሳወቁም ተነግሯል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply