ለፋኖዎች እንዲሁም ለጋዜጠኞች የተላለፈ ጥብቅ ማሳሰቢያ ========== ሸንቁጥ አየለ ========== => ፋኖዎችን በሚዲያ ላይ እየጋበዛችሁ የምታነጋግሩ ጋዜጠኞች ከዚህ ተግባራችሁ ትቆጠቡ…

ለፋኖዎች እንዲሁም ለጋዜጠኞች የተላለፈ ጥብቅ ማሳሰቢያ ========== ሸንቁጥ አየለ ========== => ፋኖዎችን በሚዲያ ላይ እየጋበዛችሁ የምታነጋግሩ ጋዜጠኞች ከዚህ ተግባራችሁ ትቆጠቡ ዘንድ ይሁን። => ፋኖዎችም በዬሚዲያዉ ላይ እየወጣችሁ የምታደርጉትን ቃለመጠይቅ አቁሙ። => ማንኛዉም የኮሚኒኬሽን ግንኙነት ከሚዲያ ላይ ሳይቀር በማሰናሰን የት እንደምትገኙ ግልጽ የጂኦሎኬሽን / የስፍራ ጥቆማ የሀሳብ መስመሮች/ መረጃ ይሰጣል። አንድ ጊዜ ያለህበትን ስፍራ የሚጠቁመዉ የጂኦሎኬሽን መረጃዉ ከተገኘ አከተመልህ። =>ፋኖዎች ሚዲያዎችን ካነጋገሩ ብኋላ በድሮን እየተመቱ መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች በስፋት እየወጡ ነዉ። ለምሳሌ ያህልም ሶስት ፋኖዎች ከአንድ ሚዲያ ጋር ቃለመጠይቅ ካደረጉ ከሰአታት ብህኋላ መገደላቸዉን ጋዜጠኛዉ እራሱ በጸጸት ” የማዝነዉ ከእኔ ጋር ቃለመጠይቅ ካደረጉ ብኋላ በመገደላቸዉ ነዉ ” ሲል ማብራራቱ ይታወሳል። ሆኖም የሚዲያዉንም ሆነ የጋዜጠኛዉን ስም እዚህ መግለጽ ያልተፈለገዉ በሁኔታዉ ላይ ጥርት ያለ መረጃ እስኪገኝ ድረስ ነዉ። ማጠቃለያ፥- ===== =>ፋኖዎች በዬ ሚዲያዉ ላይ እየቀረባችሁ የምታደርጉትን ቃለ መጠይቅ አቁሙ። ጋዜጠኞችም ፋኖውችን በዬሚዲያዉ እያቀረባችሁ የምታደርጉት ቃለመጠይቅ የፋኖዎችን ህልዉና ፈተና ዉስጥ የሚጥል ነዉና ጥንቃቄ ይደረግ። => በሀገር ቤትም ሆነ በዉጭ ሀገር ያላችሁ የፋኖ ደጋፊዎች ለፋኖዎች የትኛዉ ሚዲያ ምን እንደሆነ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ብትሰሩ ጥሩነዉ። ሚዲያ የተባለ ሁሉ ወዳጅ ሳይሆን የአቢይ ሰላዮች የሚቆጣጠሯቸዉም በርካታ ሚዲያዎች እንዳሉም መግለጫ ለፋኖዎች ስጡ። Shenkut Ayele Page

Source: Link to the Post

Leave a Reply