You are currently viewing ለፍትሓዊና መሠረታዊ የሕዝብ ጥያቄ የኃይል ምለሽ አይሰጥ!! የካቲት 13 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ ሕዝብ በመንግሥት ላይ መከፋቱንም…

ለፍትሓዊና መሠረታዊ የሕዝብ ጥያቄ የኃይል ምለሽ አይሰጥ!! የካቲት 13 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ ሕዝብ በመንግሥት ላይ መከፋቱንም…

ለፍትሓዊና መሠረታዊ የሕዝብ ጥያቄ የኃይል ምለሽ አይሰጥ!! የካቲት 13 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ ሕዝብ በመንግሥት ላይ መከፋቱንም መደሰቱንም በተለያዩ አማራጮች ሊገልጽ ይችላል፡፡ መንግሥት በበኩሉ ደስታውንም ተቃውሞውንም በልክ፣ በሕግ አግባብና ለትምህርት በሚሆን መልኩ መያዝ ይገባዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ሕዝብ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎችና የአደባባይ ተቃውሞዎች የጸጥታ ኃይሉ የሚመልስበት አኳኋን እጅጉን አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል፡፡ ችግሩ በተለይ በኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች እንዲሁም አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ላይ ጠንከር ብለውና አልፈውም ጭካኔ የተሞላባቸው መሆኑን እያስተዋልን ነው፡፡ ከሰሞኑ በደቡብ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ክልል፣ ጉራጌ ዞን፣ ወልቂጤ ከተማ ከውሐ አቅርቦት መቋረጥ ጋር በተያያዘ የከተማው ነዋሪ ውሐ ጥም ጊዜ አይሰጥምና ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ አደባባይ ወጥቶ አቅርቧል፡፡ ሆኖም የክልሉ የጸጥታ ኃይል ፍጹም ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ውሐ ጠምቷቸው የወጡ ዜጎችን ገድሏል፣ ደብድቧል፣ አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ለከፍተኛ እንግልትና ስቃይ ዳርጓቸዋል፡፡ በዚህም ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ሕይወት ጠፍቷል፡፡ የዞኑና የከተማው ማኅበረሰብ ከዚህ ቀደም ከክልል እንሁን ጥያቄ ጋር በተያያዘ እስከአኹን ካየናቸው ተቃውሞዎች ኹሉ በሰላማዊ መንገድ ጥያቄውን ሲያቀርብ እንዲሁ ሰፋ ያለ እሥርና ወከባ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ አኹንም ከዚያው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ቂምን መወጣት በሚመስል መልኩ ባዶ ጀሪካን ይዛ የወጣችን እናት የኃይል አማራጭ ተጠቅሞ የውሐ ጥም ጥያቄያቸውን በመግደል ለማርካት መሞከር የጭካኔ ጥግ ይመስለናል፡ስለሆነም 1. የዞኑና የከተማው ነዋሪ የውሐ ጥያቄ መሠረታዊ፣ ፍትሓዊና አጣዳፊ በመሆኑ በልዩ ትኩረት መልስ እንዲሰጠው አበክረን እንጠይቃለን፡፡ 2. ጥያቄያቸውንና ቅሬታቸውን በሰለማዊ መንገድ እየገለጹ የነበሩ ንጹሓንን በጭካኔ የገደሉና ያንገላቱ የጸጥታ አካላት በአፋጣኝ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን፡፡ 3. በአጠቃላይ የጸጥታ ኃይሉ (በተለይ የክልል ልዩ ኃይሎች) ኮሽ ባለ ቁጥር ግብር ከፍሎ በሚያሳድራቸው ብሎም ይጠብቁኛል ብሎ ወደሚመካባቸው ሕዝብ አፈሙዝ የሚያዞሩበት አሠራር በመሠረታዊነት እንዲፈተሽ፣ ለሕዝብ ውግንና የሌላቸው ኃይሎች ከሆኑም ተቋማቱ ተመርምረው እስከመፍረስ የሚደርስ እርማት እንዲወሰድባቸው ሕዝብ እንዲጠይቅ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ 4. ከተፈጠረው ክስተት ጋር ተያይዞ እስከአኹን አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በተገቢው መልኩ አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆናቸውና በተፈጠረው የጸጥታ ሥጋት የነዋሪዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በእጅጉ የተገታ በመሆኑ ጉዳዩ ተገቢው ትኩረት ተሰጥቶት በዞኑ የተስተጓጎለው የዜጎች ሰላማዊ እንቅሰቃሴ ወደነበረበት እንዲመለስ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡ በመጨረሻም ፓርቲያችን በሞቱት ወገኖቻችን ምክንያት የተሰማውን ልባዊ ሀዘን እየገለጸ ለተጎጂ ቤተሰቦችም መጽናናትን ይመኛል፡፡ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ እናት ፓርቲ የካቲት 13 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply