You are currently viewing ለ12 ቀናት ያህል በባህር ዳር መሀል ከተማ ላይ መንግስታዊ እገታ የተፈጸመበት አሸናፊ አካሉ ወደ 9ነኛ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዱ ታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ጥር 19 ቀን 2015 ዓ…

ለ12 ቀናት ያህል በባህር ዳር መሀል ከተማ ላይ መንግስታዊ እገታ የተፈጸመበት አሸናፊ አካሉ ወደ 9ነኛ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዱ ታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 19 ቀን 2015 ዓ…

ለ12 ቀናት ያህል በባህር ዳር መሀል ከተማ ላይ መንግስታዊ እገታ የተፈጸመበት አሸናፊ አካሉ ወደ 9ነኛ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዱ ታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 19 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸናፊ አካሉ ለ12 ቀናት ያህል ታግቶበት ከሰነበተው አባይ ማዶ ካለው የልዩ ሃይል ካምፕ ጥር 19/2015 ከምሽት ጀምሮ ወደ 9ኛ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዱ ተረጋግጧል። በአንድ ልብስ ብቻ ለ12 ቀናት ከቤተሰብ እውቅና እና ጥየቃ ውጭ በአድማ ብተና አባላት ታፍኖ መሰንበቱ ይታወቃል። አዛውንት እናቱን፣ ባለቤቱን ጨምሮ መላ ቤተሰቡ በከፍተኛ ስቃይ እና እንግልት የቆዩ ሲሆን ለጥያቄያቸውም ቀና ምላሽ የሚሰጥ አካል አልተገኘም ነበር። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) የአሸናፊ አካሉን ባለቤት ሰላም መላኩን እና ወንድሙን መ/ር ሳሙኤል አካሉን በማነጋገር ቅሬታቸውን ለህዝብ ማድረሱ ይታወቃል። አሸናፊ አካሉ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ ፍ/ቤት አልቀረበም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply