ለ2013/14 የምርት ዘመን የሚውል ከ656 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ አርሶ አደሮች መሰራጨቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ለ2013/14 የምርት ዘመን የሚውል ከ656 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ አርሶ አደሮች መሰራጨቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ለ2013/14 የምርት ዘመን የሚውል ከ656 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ አርሶ አደሮች መሰራጨቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ባሕር ዳር፡ የካቲት 25/2013 ዓ.ም (አብመድ) በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መንግሥቱ ተስፋ እንደገለፁት በዘንድሮው የምርት ዘመን 18 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ተፈጽሟል፡፡

ግዢ ከተፈፀመው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 5 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል የሚሆነው ጅቡቲ ወደብ ደርሷል፤ ከዚህ ውስጥም 5 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ማጓጓዝ ተችሏል፡፡

አጠቃላይ እንደ ሀገር ከታቀደው 18 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 31 በመቶ የሚሆነውን ማጓጓዝ ተችሏል ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡

በአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ዙሪያ የተከናወኑ ሥራዎች

• ወደ ሀገር ውስጥ ከገባው 3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሕብረት ሥራ ማኅበራት ተጓጓዟል፤ ይህም 50 በመቶ ይሸፍናል፡፡

• አጠቃላይ ወደ ሕብረት ሥራ ማኅበራት ከተጓጓዘው ውስጥ 16 ነጥብ 8 በመቶ የሚሆነውን ለአርሶ አደሮች ማቅረብ ተችሏል፡፡

• ለአርሶ አደሮች 656 ሺህ 768 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ተሰራጭቷል፡፡

• የዘንድሮው ጥቅል የአፈር ማዳበሪያ መጠን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ3 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል ብልጫ አለው፡፡

• በዘንድሮው ዓመት የአፈር ማዳበሪያ ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት መንግሥት 4 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ድጎማ በማድረግ የአፈር ማዳበሪያ ግዥ ተፈፅሟል፡፡

በቅርብ ጊዜ ውስጥም ሁሉንም የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ለአርሶ አደሮች በወቅቱ እንዲደርስ ይደረጋል ብለዋል አቶ መንግሥቱ ፡፡

ባለፉት ዓመታት በአፈር ማዳበሪያ ግዢና የማጓጓዝ ሥራ ላይ ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን በመለየት እንዲሁም ውጤታማ ሥራ የሠሩና ትልቅ ሚና የተጫወቱ ባለድርሻ አካላትን የማመስገንና እውቅና የመስጠት ሥራ እንደተከናወነም አቶ መንግሥቱ ጠቅሰዋል፡፡

“ለ2013/14 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ ለአርሶ አደሮች እንዲደርስ የሚያስችል ሥራ እየተሠራ ነው” ብለዋል፡፡

ምንጭ፡- ግብርና ሚኒስቴር

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

The post ለ2013/14 የምርት ዘመን የሚውል ከ656 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ አርሶ አደሮች መሰራጨቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ first appeared on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.

Source: Link to the Post

Leave a Reply