ለ30 ሺህ ዜጎች ነፃ የህክምና ምርመራና የምክር አገልግሎት የሚሰጥ ጤና ኤክስፖ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነዉ ተባለ

ኤፍ ዚ ማርኬቲንግ እና ኮምኒኬሽን ለሶስት ቀናት የሚቆይ አፍሮ ኤዥያ አለም አቀፍ የጤና ኤክስፖ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ከግንቦት 9-11ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳል ብሏል፡፡
ከ30 ሺ በላይ ለሚሆኑ ጎብኚዎች ነፃ የጤና ምርመራ እና የምክር አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ታዉቋል፡፡

ለኤክስፓው አፍሮ -ኤዥያ የሚለው ስም መመረጡ ኢትዮጵያ ከአፍሪካም ሆነ ከኤዥያ ጋር ያላትን ጂኦግራፊያዊ ፣ ታሪካዊ እና ባህልዊ ትስስር ያለንን እውቅና ስለሚያሳይ መሆኑ ተነግሯል።

ስያሜው አፍሪካን እስያ ላይ አፅንኦት ቢሰጥም ኤክስፓው አለማቀፋዊ ነዉ ተብሏል፡፡

ኤክስፓው ከሀገራችን እና ከተለያዮ የአለማችን ሀገሮች የተውጣጡ ከ400 በላይ የጤና ተቋማትን ፣ የኢንዱስትሪ ባለሙያዎችን ባለድርሻ አካላት የሚሳትፍ ነ፡፡

እውቀት ለመለዋወጥ ፣ትብብርን ለማጎልበት እና የላቀ የጤና አጠቃቀም መፍትሄዎችን ለማሳየት በርካታ ነፃ ምርመራዎችን ለማህበረሰባችን ለመስጠት ያለመ መሆኑ ታወቋል፡፡

ኤፍ ዚ ማርኬቲንግ እና ኮምኒኬሽንስ ኃ. የተ. የግ. ማ በኢትዮጵያ የግብይት እና የኮምኒኬሽን ዘርፍ ከአስር አመት በላይ ያስቆጠረ ድርጅት መሆኑንም ሰምተናል፡፡

ሐመረ ፍሬው

ሚያዚያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply