You are currently viewing ለ6 ወራት ተዘግቶ የነበረው የኢትዮ-ሱዳን መንገድ ከነገ ጀምሮ ሊከፈት መሆኑ ተገለጸ ታህሳስ 26/2014/አሻራ ሚዲያ/ በዛሬው እለት የኢትዮጵያ እና የሱዳን ወታደራዊ አመራሮች እና የሁለቱ…

ለ6 ወራት ተዘግቶ የነበረው የኢትዮ-ሱዳን መንገድ ከነገ ጀምሮ ሊከፈት መሆኑ ተገለጸ ታህሳስ 26/2014/አሻራ ሚዲያ/ በዛሬው እለት የኢትዮጵያ እና የሱዳን ወታደራዊ አመራሮች እና የሁለቱ…

ለ6 ወራት ተዘግቶ የነበረው የኢትዮ-ሱዳን መንገድ ከነገ ጀምሮ ሊከፈት መሆኑ ተገለጸ ታህሳስ 26/2014/አሻራ ሚዲያ/ በዛሬው እለት የኢትዮጵያ እና የሱዳን ወታደራዊ አመራሮች እና የሁለቱ ሀገራት አጎራባቸው አስተዳደሮች ማለትም የምራብ ጎንደርና በሱዳን በኩል ደግሞ የጋላባት አካባቢ አስተዳደር ተወካዮች በመተማ ከተማ ተወያይተዋል፡፡ የመተማ ከተማ ከንቲባ አቶ ሀብቴ አዲሱ ለአል ዐይን አማርኛ እንደተናገሩት ሐምሌ 17፣2013ዓ.ም የመተማ-ጋላባት መንገድ በሱዳን በኩል ተዘግቶ ነበር፡፡ የሱዳን መንግስት መንገዱን የዘጋው አንድ ወታደራዊ አመራር በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ተገድሎብኛል ብሎ በማሰቡ መሆኑን አቶ ሀብቴ ተናግረዋል፡፡ ከንቲባው እንዳሉት መንገዱ አለምአቀፍ መስመር ስለሆነ እንዲከፈት በአካባቢው አስተዳደር እና በሀገር ሽማሌዎች ለማስከፈት ጥረቶች ሲ…ደረጉ ቆይተዋል፡፡ በስብሰባው ላይ መንገዱ ተክፍቶ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ እንዲቀጥል መግባባት ላይ መደረሱን የገለጹት አቶ ሀብቴ ከዚህ በተጨማሪም ለሁለቱ ሀገራት አለመግባባት ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችም ተነስተዋል ብለዋል፡፡ በሱዳን ግዛት የሚንቀሳቀሱ የህወሓት ኃይሎች መኖራቸውንና ያሉበትን ቦታ ጭምር በመጥቀስ እና ትክክል እንዳልሆነ ለሱዳን ወታደራዊ አመራር እንደተነገራቸው ከንቲባው ተናግረዋል፡፡ ሱዳን በግዛቷ ውስጥ ለህወሓት ሃይሎች ከለላ በመስጠት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ጥቃት እንዲሰነዝሩ ማስተባበሯ አይዘነጋም። ኢትዮጵያ እና ሱዳን በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚያደርጉት ድርድር በተለያየ ጊዜ ቅራኔ ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply