ለ95 አመታት ያክል ጸጉራቸውን ያልተቆረጡት አዛውንት ጸጉራቻው የገቢ ምንጭም ሆኖላቸዋል፡፡ሳይቆረጥ ለአንድ ክፍለ ዘመን የተጠጋው የአዛውንቱ የጸጉር እርዝማኔ 24 ጫማ ወይም 7 ነጥብ 3 ሜት…

https://cdn4.telesco.pe/file/FjErdydnBldA1V68ltP0OjDwArF0PFaGQ9dorfs2g8RTTWAZNZfTyQgHcNEncrRJj_eIrDRGWSRyPmoJ9NMKypgGdhpfMQB8Te-tZlCFZxQZ-JkPsWyK7rxKekCdrDfPMH8XIHM7x1FPhz75qkSw_LQGKSgez91YvBTyRAsriyEYJHf4w4yyVDD32Za-TneAO0zG70eiq4WBzNChtTl5dGp2gXFmZV6ZEfCpYJPCTzInpVhTIiaaVbw1teJOstmQ7PUjJbwqGfV07zIIvWnE9alpR0ePokjqyBMNYTv__tpjo8_7JwYo3mwLVlBFfaPuvZvS9nLf5DkE8rTXwE7iEQ.jpg

ለ95 አመታት ያክል ጸጉራቸውን ያልተቆረጡት አዛውንት ጸጉራቻው የገቢ ምንጭም ሆኖላቸዋል፡፡

ሳይቆረጥ ለአንድ ክፍለ ዘመን የተጠጋው የአዛውንቱ የጸጉር እርዝማኔ 24 ጫማ ወይም 7 ነጥብ 3 ሜትር እንደሚረዝም ታውቋል፡፡

በህንድ ገጠራማው አካባቢ የሚኖሩት እኚህ አዛውንት ጸጉራቸው ለምን እንዳሳደጉ ለራሳቸው እንኳን አልገባቸውም ነው የተባለው፡፡

ጸጉራቸውን ያሳደጉበትን ምክንያት ያልገባቸው እኝህ አዛውንት አሁን ላይ ጸጉራቸው ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እንደሆነላቸው ነው የተነገረው፡፡

ከህንድ ዋና ከተማ ኒውዴልሂ አንስቶ ከተለያዩ ሀገራት የእኝህን አዛውንት ጸጉር ለማየት ጎብኝዎች እንደ ጉድ እየጎረፉ ነውም ተብሏል፡፡

አዛውንቱን ከሚጎበኙ ቱሪስቶች መካከልም ሴቶች ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዙ ነው የተገለጸው፡፡

አበው ሲመርቁ ጧሪ ቀባሪ አያሳጣህ ይላሉ ህንዳዊው አዛውንት በእርጅና እድሜያቸው ጸጉራቸው እየጦራቸው ነው ሲል ብሎለቸዋል ለየት ያሉ ክስተቶችን በመዘገብ የሚታወቀው ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡

በጅብሪል ሙሀመድ
ሕዳር 13 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply