ሊቨርኩዘን- አዲሱ የቡንደስሊጋ አሸናፊ!አሎንሶ ባየር ሊቨርኩዘንን  የቡንደስሊጋው ዋንጫ አሸናፊ አደረገ። ይህንን ማድረግ የቻለ የመጀመሪያው አሰልጣኝ ሆኗል።‘Neverkusen’  የሚለው ቅጽ…

ሊቨርኩዘን- አዲሱ የቡንደስሊጋ አሸናፊ!

አሎንሶ ባየር ሊቨርኩዘንን  የቡንደስሊጋው ዋንጫ አሸናፊ አደረገ። ይህንን ማድረግ የቻለ የመጀመሪያው አሰልጣኝ ሆኗል።

‘Neverkusen’  የሚለው ቅጽል ስማቸውም  ከእንግዲህ ወዲያ ዋጋ አጣ።

ተጨማሪ ዋንጫዎችን ሊያሸንፉ የሚችሉበት ዕድል አለ። ከቡንደስሊጋው የሚልቅ ግን የለም።

በ1992-93 ካሸነፉት ዲኤፍቢ-ፖካል በኋላ የመጀመሪያ ዋንጫቸው ነው። ለ11 የውድድር ዘመናት የዘለቀው የባየርን ሙኒክ የበላይትም ተቋጨ።

የዣቢ አሎንሶ ትዕግስት ያስገርማል። የማድሪድን ከ14 ዓመት በታች ቡድን ከመረከቡ በፊት እንኳን ዋናውን ቡድናቸውን እንዲያሰለጥንላቸው የጠየቁት ክለቦች ነበሩ።
እርሱ ግን አልተጣደፈም። ቀስ ብሎ መማርን መረጠ።

የሪያል ሶሲዬዳድን “ቢ” ቡድን ‘Sanse’ ለሶስት ዓመታት አሰልጥኗል። ብዙዎች ከጠበቁት በላይ በዚያ ቆይቷል። አሎንሶ በSanse ቡድኑን ከ1960ዎቹ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሴጉንዳ ዲቪዥን አሳድጓል። በዚያ የውድድር ዘመን ቦሩሲያ ሞንቼግላድባክ ያቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ። እንዲያውም የኮንትራት ማራዘሚያ ተፈራረመ።

በግንቦት 2022  Sanse ወደ ሶስተኛው ሊግ መውረዱ እርግጥ ሲሆን እና ኢማኖል አልጉአሲ ወደ ዋናው ቡድን ሊያድግ የሚችልበትን መንገድ ሲዘጉበት አሎንሶ ከክለቡ ተለያየ።

በድጋሜ በትዕግስት ትከክለኛውን ኋላፊነት ተጠባበቀ። በወራጅ ቀጠና ከመፍገምገም የሚያወጣው አሰልጣኝ በመፈለግ ላይ የነበረው ባየር ሊቨርኩዘን ጠራው። ኋላፊነቱን ከተረከበ በኋላ ያደረገውን የእግር ኳሱ ዓለም በሚገባ ተመልክቷል።

አቤል ጀቤሳ

ሚያዚያ 6 2016

Source: Link to the Post

Leave a Reply