ሊቨርፑል ከዩሮፓ ሊግ ውጪ ሆነ የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ከአታላንታ ጋር ያደረገውን የዩሮፓ ሊግ ሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ቢችልም ወደ ቀጣዩ ዙር መሻገር ሳይች…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/SY-M8JMvRhFI_PQCwAb0rkcQMRW3huOAfuwzkgZfqgbP5c6NU09M94ZkoHD_gD0n9F3ssHn5rQhVpd_K6YNwm3rp3LSKLES5mzqwF74RB5g5qEK7askzE4wbSHrSBrGJBVJ3uGP-Pf3ZyYbib-kLKgb2gBH8JPDVW1X33UAnzgjnHfcdgpA4HC7uToqaE7R1ZM_TsKQSEj4zjmoQj1SJ2QKIYYsJn1wQYopCdK_de2BvHfrBkwdqjmAecs-6OcOa0xY0ME-hnZJzjWqp5q0ARLtVlxtols3UxlVWOCol2XvVgz4iZIf4Zt8O_dKwtEuf84XzyhpsKdySHnpRSYSleQ.jpg

ሊቨርፑል ከዩሮፓ ሊግ ውጪ ሆነ

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ከአታላንታ ጋር ያደረገውን የዩሮፓ ሊግ ሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ቢችልም ወደ ቀጣዩ ዙር መሻገር ሳይችል ቀርቷል።

የሊቨርፑልን የጨዋታው የማሸነፊያ ግብ መሐመድ ሳላህ በፍፁም ቅጣት ምት ማስቆጠር ችሏል።

አታላንታ ሊቨርፑልን በድምር ውጤት 3ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

ባየር ሊቨርኩሰን ከዌስትሀም ጋር 1ለ1 ቢለዩም የመጀመሪያውን ዙር 2ለ0 ማሸነፉን ተከትሎ በድምር ውጤት አሸንፎ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል።

ሮማ በበኩሉ ኤሲ ሚላንን የሁለቱንም ዙር ጨዋታዎች በማሸነፍ 3ለ1 በሆነ የድምር ውጤት ረቶ ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀል ችለዋል።

በግማሽ ፍፃሜው ባየር ሊቨርኩሰን ከሮማ እንዲሁም አታላንታ ከማርሴይ ጋር ይጫወታሉ።

ሚያዚያ 11ቀን 2016 ዓ.ም

ኤትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጲያዊያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply