
#ሊዮኔል ሜሲ በኢትዮጵያ ዐይነ-ስውራንን ለመደገፍ ከኦርካም ቴክኖሎጂ ጋር በትብብር ለመሥራት ተስማማ ጥር 8 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ኮከብ ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ በኢትዮጵያ የሚገኙ ዐይነ-ስውራን ዜጎችን ለመደገፍ ከኦርካም ቴክኖሎጂ ጋር በትብብር ለመሥራት ተስማምቷል። ተጫዋቹ በኢትዮጵያ የሚገኙ ዐይነ ስውራን ዜጎችን ለመደገፍ በመስማማቱም ክብር እንደሚሰማው በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አስታውቋል። የኦርካም ቴክኖሎጂ በሺህዎች የሚቆጠሩ ዐይነ ስውራንን ሕይወት እያሻሻለ ያለው ሊዮኔል ሜሲ፣ ቴክኖሎጂው ዐይነ ስውራን ሕልሞቻቸውን እንዲያሳኩ ይረዳቸዋል ብሏል። የቀዳማዊ እመቤት ጽ/ቤት በቅርቡ የዘመኑ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆነ “OrCam MyEye” የተሰኘ ዐይነ ስውራንን የሚያግዝ መነፅር ለሁለት ሺህ ዐይነ ስውራን አስረክቧል። መሣሪያው አማርኛም ሆነ እንግሊዝኛ የሚያነብብ ሲሆን የገንዘብ ኖቶችን ለይቶ ለተጠቃሚው ያስረዳል፤ የቀለም ዓይነትን ይለያል እንዲሁም ከፊት ለፊት ምን እንዳለ እና ማን እንደመጣ መዝግቦ በመያዝ መረጃ ይሰጣል። 2 ሺህ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚ ያደርጋል::ሜሲ አክሎ ሲናገርም በዚህም ይህን በማድረጌ በጣም ደስ ብሎኛል ብሏል:: የተሰጣቸውም ኢትዮጵያውያን ድጋሚ እንደተወለድኩኝ ነው የምቆጥረው ሲሉ በደስታ ተናግረዋል ነው የተባለው። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post