
ሊዲያ በትምህርት ቤት ውስጥ በራሷ መንገድ ለመሄድ መሞከሯ እና “ሌሎች የሚሉትን ሁሉ መቀበል” አለመፈለጓ በሌሎች ነቀፋ እንዲቀርብባት፣ ዘለፋን እንድታስተናግድ መነሻ ሆኗል። በትምህርት ቤቱ ተጽዕኖ እንዳላት ከሚነገር ተማሪ ጋር በነበራት አለመግባባት ምክንያት አብዛኛው ተማሪ ከእርሷ ጋር ጓደኛ ለመሆን አይፈለግም ነበር። በዚህም ምክንያት “ምንም የተለየ ነገር ሳይኖረው” በአለባበሷ፣ በጸጉር አሰራሯ ‘በማሾፍ’ ሌሎች ተማሪዎች እንዲስቁ እርሷ ደግሞ እንድትሸማቀቅ ይደርግ እንደነበር ታስታውሳለች።
Source: Link to the Post