ላለፉት በርካታ ዓመታት ከአቸፈር፣ሻውራ፣ ደለጎ፣ መተማ 4 ወረዳዎችን ለማገናኘት ይሰራል እየተባለ የተነገረለት መንገድ ከተራ ፕሮፖጋንዳ አልፎ መሬት ላይ እስካሁን ባለመታየቱ በማህበረሰቡ ዘን…

ላለፉት በርካታ ዓመታት ከአቸፈር፣ሻውራ፣ ደለጎ፣ መተማ 4 ወረዳዎችን ለማገናኘት ይሰራል እየተባለ የተነገረለት መንገድ ከተራ ፕሮፖጋንዳ አልፎ መሬት ላይ እስካሁን ባለመታየቱ በማህበረሰቡ ዘን…

ላለፉት በርካታ ዓመታት ከአቸፈር፣ሻውራ፣ ደለጎ፣ መተማ 4 ወረዳዎችን ለማገናኘት ይሰራል እየተባለ የተነገረለት መንገድ ከተራ ፕሮፖጋንዳ አልፎ መሬት ላይ እስካሁን ባለመታየቱ በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ መፍጠሩ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 23 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከአማራ ሚዲያ ማዕከል ጋር ቆይታ ያደረጉት የአቸፈር፣ሻውራ፣ ደለጎ፣ መተማ የመንገድ ልማት ጠያቂ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ግሩም ምሳሌ የማህበረሰቡን ቅሬታ ገልፀዋል። የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ግሩም ምሳሌ ከአቸፈር፣ሻውራ፣ ደለጎ፣ መተማ ድረስ የሚያገናኘው የመንገድ ልማት መቼ እንደሚጀምርና መቼ እንደሚጠናቀቅ ግልፅ የሆነ መረጃ እየተሰጠን አይደለም ብለዋል። ኮሚቴው ከ5 ወራት በፊት በህዝቡ ይሁንታ የተመሰረተ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ግሩም ለብዙ ዓመታት ቃል እየተገባ በተግባር መሬት ላይ ልናገኘው ባለመቻላችን የሚመለከተው የመንግስት አካል አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥበት ተፅዕኖ ለመፍጠር፣ ትክክለኛ እቅዱን አውቆ ሁሉንአቀፍ ትብብር ለማድረግ ጭምር መቋቋሙን ገልፀዋል። ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ይህ ደቡብና ሰሜን አቸፈር እንዲሁም ሻውራና ደለጎን ለማገናኘት የታለመለበት መንገድ እስካሁን ድረስ አለመሰራቱ ቅሬታ ፈጥሮብናል ብለዋል የኮሚቴው ሰብሳቢ። በተደጋጋሚ እየተዋሸ የከረመው የመንገድ ልማት ሳይሰራ ላለፉት 3 ምርጫዎች ለተራ ፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ብቻ መዋሉን ነው የጠቀሱት። በ4ቱም ወረዳዎች ህዝብ ግፊት ኮሚቴው መቋቋሙን የገለፁት አቶ ግሩም እስካሁን 6 ያህል ህዝባዊ ምክክሮችን መደረጋቸውን አስታውቀዋል። አብይ ኮሚቴው 21 አባላት፣ ንዑስ ኮሚቴዎች ደግሞ በእያንዳንዱ 7 በድምሩ 28 አባላት እንዳላቸው የተገለፀ ሲሆን የአካባቢው ማህበረሰብም በሀሳብም ይሁን በገንዘብ ከኮሚቴው ጎን ቆሞ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ በመግለፅ በርቱ ያላቸው ስለመሆኑ ነው አቶ ግሩም የተናገሩት። መንገዱ አቋራጭ ከመሆኑም ባሻገር በመካከል የሰሊጥ ምርትን እሴት ጨምሮ ወደ መሀል ሀገር በቀላሉ ለማድረስ፣ ብዙ ያልተጎበኙ የቱሪስት መስህብ ሀብቶች እንዲጎበኙ እድል ይሰጣል፣ በዚህም ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል። አካባቢው ከዚህ በፊት ተጎድቶ የቆዬ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ግሩም አሁን ላይ ለ4ቱም ወረዳዎች ማለትም ለሰሜን አቸፈር፣ ለደቡብ አቸፈር፣ለአለፋ እና ለቋራ ወረዳዎች ለህዝባዊ ኮሚቴው እውቅና እንዲሰጡት በደብዳቤ መጠየቃቸውንና በዚህም የአለፋ ወረዳ ቀድሞ ሰላማዊ የሆነውን ጥያቄ እውቅና በመስጠት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግልንም በደብዳቤ አሳውቆናል፤ እናመሰግናለን ብለዋል። በአጠቃላይ የፌደራል መንገዶች ባለስልጣን በመንገድ ልማቱ ዙሪያ ተገቢ እና ግልፅ መረጃ በመስጠት በተግባር ወርዶ መንገዱ እንዲሰራ እንዲያደርግ የጠየቀው ኮሚቴው ስራ ሲጀምር ወሰን ከማስከበርና ግምት ከመስጠት ጋር በተያያዘ ለማገዝ ፈቃደኛ መሆኑን ገልጾ ካልሆነ ግን ሰላማዊ ሰልፍ ለመጥራት የሚገደድ ስለመሆኑ ነው ያስታወቀው። የአማራ ሚዲያ ማዕከል ስለጉዳዩ ለማጣራት የፌደራል መንገዶች ባለስልጣንን በቢሮ ስልክ ለማግኘት በሚል በተደጋጋሚ ያደረገው ጥረት የሚጠራ ስልካቸው ባለመነሳቱ ለጊዜው አልተሳካም፤ እንዳገኘ ምላሻቸውን አካቶ የሚመለስ ይሆናል። ከኮሚቴው ሰብሳቢ ከአቶ ግሩም ምሳሌ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ የምናጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply