You are currently viewing ላለፉት 4 ዓመታት በኦሮሚያ ክልል በተለይም በምስራቅና በምዕራብ ወለጋ፣ በምዕራብና ምስራቅ ሸዋ ዜጎች በነጻነት የመኖር መብታቸው ስለተነፈገ ክልሉ በኮማንድ ፖስት እንዲተዳደር እንዲደረግ ሲል…

ላለፉት 4 ዓመታት በኦሮሚያ ክልል በተለይም በምስራቅና በምዕራብ ወለጋ፣ በምዕራብና ምስራቅ ሸዋ ዜጎች በነጻነት የመኖር መብታቸው ስለተነፈገ ክልሉ በኮማንድ ፖስት እንዲተዳደር እንዲደረግ ሲል…

ላለፉት 4 ዓመታት በኦሮሚያ ክልል በተለይም በምስራቅና በምዕራብ ወለጋ፣ በምዕራብና ምስራቅ ሸዋ ዜጎች በነጻነት የመኖር መብታቸው ስለተነፈገ ክልሉ በኮማንድ ፖስት እንዲተዳደር እንዲደረግ ሲል ሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህበር ጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 26 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህበር በወቅታዊ የሀገራችን ሁኔታ የተሰጠ መግለጫ:_ በሀገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት 30 እና ከዚያ በላይ ዓመታት በተለይም ደግሞ ኢሕአዴግ ወደ ብልጽግና ስሙን ከቀየረበት ካለፉት ሪ ጥቃት ጀምሮ የአማራ ብሔር ተወላጆችና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የኾነትን በኦሮሚያ ክልልና በቤንሻንጉል ክልል በተለይም በምስራቅና በምዕራብ ወለጋ፣ በምዕራብና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች እና በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ በነፍስ በላዎች ክቡር የኾነው የሰው ዘር ታስቦበትና ታቅዶበት መዋቅራዊ በሆነ የዘር ፍጅት የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑ ተለይተው በጅምላ ተጨፍጭፈው በግሬደር ሲቀበሩ እና ህዝባችን የመንግስት ያለኽ ብሎ በመቃወምና የመጠቃቱን ልክ አቤቱታውን ለመንግስት ቢያቀርብም የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር በእንደራሴ ምክር ቤቱ ተገኝተው ተሸናፊዎች ሰው ሲገድሉ በሞቱት ሰዎች መቃብር ላይ ለጥላቸው እኛ በምትኩ ችግኝ እንተክላለን በማለት በህዝባችን መጨፍጨፍ ሲዘብቱበትና ሲቀልዱበት እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው። በተመሳሳይ ኹኔታ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ዋና አስተዳዳሪም በመስቀል አደባባይ ላይ ነፍጠኞች ቅስማችንን በሰበሩበት ቦታ ላይ ኾነን እንዳይመለሱ አድርገን ሰባበረናችዋል፤ ከአባይ ማዶ ተሻግረን ቁማሩን በልተነዋል፣ ብልጽግናን ያቋቋምነው ለአንድ ማህበረሰብ ጥቅም ለማስከበርና እንዲመች ለማስቻል ብለን ያቋቋምነውና ሌላም ሌላም ጥላቻ የበዛበት ንግግራቸው ዛሬ ላይ በኦሮሚያ ክልል እየደረሰ ላለው የአማራ ብሄር የዘር ፍጅት የመጀመሪያውና ዋናው ተጠያቂ የክልሉ ፕሬዝዳንትና በተዋረድ ያለው የክልሉ ባለስልጣናት ናቸው። የአንድ ሀገር መንግስት ለኹሉም ዜና ማህበረሰብ ለችግሮችም ኾነ ለመልካም አጋጣሚዎች ኹሉንም በእኩልነት የማስተዳደርና ሚዛናዊ መኾን እንደሚጠበቅበት ኹሉ በየደረጃው ያሉ የመንግስት ሹማምንቶች በሚያሳዩት ግዴለሽነት ግፈኞችና ጨፍጫፊዎች የልብ ልብ ተሰምቷቸዋል። ሃገሬ ብሎ ቤተሰብ መስርቶ፣ ሃብት ንብረት አፍርቶ የሚኖርውን የአማራ ብሔር የኾኑትን ሕጻናትን፣ እናቶችንና አሳ ደካማዎችን በጅምላ መጨፍጨፍ በሕግም ኾነ በማንኛውም መልኩ የማያስጠይቅ እንደልኾነ እስከሚመስላቸውና በማናለብኝነት በኦሮሚያ ክልል የሚኖረውን ህዝባችንን ላለፉት አራት ዓመታትና ከዚያ በላይ በጅምላ ጭፍጨፋው እንዲቀጥልና ህዝባችን እንዲፈናቀል፣ የሀገሪቱ ሕገ መንግስት አለመሻሻሉና የፌደራል መንግስት የሀገሪቱን ህዝብ በእኩል አይን ያለማየትና የተረኝነት አስተሳሰብ ያለበት አስተዳደር መኾኑ ነው፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እርምጃዎች እንዲወስድ እንጠይቃለን:_ 1) ባለፉት ፬ ዓመታት በተደጋጋሚ ጊዜ በኦሮሚያ ክልል በወለጋ ክፍለ ሀገር (ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፤ በምስራቅና ምዕራብ ሸዋ፣ በሰሜን ሸዋ ደራ ወረዳ የአማራ ብሔርና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ጭፍጨፋዎችን ሲመሩና በድርጊቱ ሲሳተፉ የነበሩ ኹሉም አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ 2. ላለፉት 4 ዓመታት በኦሮሚያ ክልል በተለይም በምስራቅና በምዕራብ ወለጋ፣ በምዕራብና ምስራቅ ሸዋ ዜጎች በነጻነት የመኖር መብታቸው ስለተነፈገ ክልሉ በኮማንድ ፖስት እንዲተዳደር እንዲደረግ፣ 3 በእንደራሴ ምክር ቤት (ፓርላማ) በአሸባሪነት የተፈረጀው የኦነግ አመራሮች በመንግስት መዋቅር ውስጥ የሽብር ቡድኑን የሚደግፉ ስላሉ የብልጽግና መንግስት እራሱን ፈትሾ ለሕግ እንዲያቅርብ፣ 4. የሀገሪቱ መንግስት ከተረኝነት ስሜት ወጥቶ ሁሉንም ክልሎች በእኩልነት እንዲያስተዳድር እንዲደረግ፣ 5. ኢትዮጵያዊነት አቀንቃኞችን አሳድዶ በመያዝ እስር ቤት ውስጥ በማጎርና ኢትዮጵያዊነት በየመድረኩ በአፍ መደስኮር አይቻልምና ኢትዮጵያን ስለወደዱ ማፈኞችን ስላወና ስለተጸየፉ ብቻ በየ እስር ቤቱ እየማቀቁ ያሉ ኩሩ ኢትዮጵያውያንን ለኢትዮጵያ ክብር ሲባል በአስቸኳይ ከየ እስር ቤቱ እንዲለቀቁ፣ 6. በኦሮሚያ ክልል እስከ አኹን ለተጨፈጨፉት የአማራ ብሔርና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ኹሉ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የስልጣን መዋቅር በተለይም የክልሉ የፀጥታ መዋቅርና አካላት አንድን ብሔር መሰረት ያደረገ የዘር ፍጅት ሲካኺድ የዜጎችን ሕይወት ባለመታደጋቸው ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply