ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ዓይነት ያልተገባ ቅስቀሳ የህዝቦችን አንድነት ይጉዳል!!! የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ******** ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) የአማራው አን…

ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ዓይነት ያልተገባ ቅስቀሳ የህዝቦችን አንድነት ይጉዳል!!! የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ******** ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) የአማራው አንገት አንድ ነው፡፡ ጎጃም ፣ሽዋ፣ ጎንድር እና ወሎ የሚሉ መጠሪያዎች በአንድ ሰው ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ክፍሎች ስያሜ ዓይነት ናቸው፡፡ በመሆኑም የአማራው አንገት አንድ ነው፡፡ በዚህ የተነሳ ህመሙ የሁሉም ነው፡፡ ለአጋጠመን ህመም መፈውሻ መድህኒት የምንፈልገው በጋራ ነው፡፡ አንዳችን ያለ ሌላችን ዋስትናም ሆነ ውብት የለንም፡፡ … በትግራይ ወራሪ ሀይል አማካኝነት በክልላችን የታቃጣውን ውስጣዊና ውጫዊ ወረራ ለመመከት በቀደሙ ዓይቶቻችን የክተት ጥሪ ዓይነት አክተን ዘመተናል፡፡ በየግንባሩ ለአማራ ክብርና ነፃነት ሲባል ወድ መስዋዓትነት ከፍለናል፡፡ ይህ ደግሞ ለመጪው ትውልድ የታሪክ አሻራ በመሆኑ አይቆጨንም ፤አይፅፀትንም፡፡ በመሆኑም ትግላችን ወደፊት ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ይህ ቃላችን የበላይ ዘለቀ ፣የእምዬ ምኒልክ ፣የመይሳው ቴዎድሮስ እና የንጉስ ሚካኤል የማይታበል ቃል ነው፡፡ ዳሩ ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ ጦር ከፈታው ይልቅ ወሬ የፈታው እንዲሉ የባህር ዳር ከተማ አስተዳድር ፀጥታ ምክር ቤት መልዕክት ተከትሎ የህዝቦችን አንድነት ለማላላት እና የጀመረነውን የህልውና ትግል ጥላሽት ለመቀባትና የጠላት መሳሪያ ለመሆን የተለያዩ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ዓይነት ዘመቻ አስተውለናል፡፡ ከሰሞኑ የከተማውን ህዝብ ሰላምና ደህንነት ከሰርጎገቦች ለመጠበቅ ሲባል እየተወሰዱ ባሉ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎች ተከትሎ አንዳንድ ተገቢ ያልሆኑና የባህርዳርን ህዝብ እና ከተማን የማይመጥኑ የስም ማጠልሸትና የከተማዋን መልካም ስምና ገፅታን የማበላሸት አላማ ያላቸው ሀይሎች ያልተገባና በአንድ በኩል እውነትነት የሌለው በሌላ በኩል ደግሞ የህዝቦችን አንድነት የሚያዳክሙ ቅስቀሳዎችን እየተመለከትን ነው። ይህ ደግሞ አማራ በአንድነት ለጀመረው የህልውና ዘመቻ አደናቃፊ ነውና ከድርጌታችው ሊቆጠቡ ይገባል፡፡ የባህር ዳር ከተማ አስተዳድር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተጠቅሞ የከተማውን ህዝብ ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ እና በጦርነቱ ተፈናቅለው የሚገኙ ወንድሞቻችንን ከሰርጎገቦች ለመጠብቅ ሲል የተለያዩ ወሳኔዎች ወስኗል፡፡ ይህ ደግሞ የጋራ ድህንነት ነው፡፡ ተፈናቃዩችን በተመለከተ በአንድ ማዕከል እንዲቀመጡ ተጠየቅ እንጂ ማንም ከቤቱ ይውጣ አልተባለም፡፡ ባህር ዳር እኮ የሁሉም ቤት ነች፡፡ ቤታችንን ደግሞ ከጠላት መጠበቅ የሁላችንም ሀላፊነት ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ባህርዳር እኮ አይደለም በጦርነት ተፈናቅለው ለከተሙባት ወገኖቿ ቀርቶ እዛው በጦርነቱ አውድማ ለችግር የተጋለጡትን ቦታው ድረስ ተገኝታ ከለበሰችው አልብሳ፤ ከምትበላውም አካፍላ ለወገን ደራሽነቷን በተግባር ያረጋገጠች የሁላችንም መኮሪያና አቃፊ ከተማ ነች። በዚህ አጋጣሚ የባህር ዳርን ህዝብ በተለይም ወጣቶች ለነበራችሁ የላቀ አጋርነትና ድጋፍ የባህር ዳር ከተማ አስተዳድር አመራር እጅ በመነሳት ምስጋና ያቀርባል፡፡ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply