ላየን ኢትዮጵያ በሆቴል ቱሪዝምና ቢዝነስ የትምህር ዘርፎች ያስለጠናቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
ኮሌጁ በዛሬው ዕለት 5 መቶ 57 ተማሪወችን ነው ያስመረቀው።
ላየን ኢትዮጵያ በሆቴል ቱሪዝምና ቢዝነስ ዘርፎች ላለፉት 20 ዓመታት ሲያሰለጥን የቆየ የትምህርት ተቋም ነው።
የኮሌጁ መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ መሃመድ አወል፣ ላየን ኢትዮጵያ በሆቴል ቱሪዝምና ቢዝነስ ዘርፎች ትኩረት ሰጥቶ መስራቱን ይቀጥላል ብለዋል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት፣በአዲስ አበባ የባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አማካሪ ዶክተር ፍፁም አባተ በበኩላቸው ፣
ዘርፉ አሁንም ያልተነካ የስራ መስክ በመሆኑ በስፋት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
በዘርፉ የሚሰለጥኑ ተማሪዎችን ከሀገር ውስጥ አልፎ በተለያዩ ሀገራት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማብቃት እንደ ሀገር ያስፈልጋል ብለዋል።
ኮሌጁ ላለፉት 20 ዓመታት ከ 11 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አሰልጥኖ ማስመረቁን አስታውሷል ።
በአባቱ መረቀ
ጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video