“ሌሎች ለጥፋትና አገር ለመበተን ይደራጃሉ እኛ ደግሞ ራሳችንና አካባቢያችን ለመጠበቅ ስንደራጅ የነበረብን ተፅዕኖ መደገም የለበትም” ሲል ፋኖ አይሸሽም ዮሃንስ አሳሰበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/…

“ሌሎች ለጥፋትና አገር ለመበተን ይደራጃሉ እኛ ደግሞ ራሳችንና አካባቢያችን ለመጠበቅ ስንደራጅ የነበረብን ተፅዕኖ መደገም የለበትም” ሲል ፋኖ አይሸሽም ዮሃንስ አሳሰበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/…

“ሌሎች ለጥፋትና አገር ለመበተን ይደራጃሉ እኛ ደግሞ ራሳችንና አካባቢያችን ለመጠበቅ ስንደራጅ የነበረብን ተፅዕኖ መደገም የለበትም” ሲል ፋኖ አይሸሽም ዮሃንስ አሳሰበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 8 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በጎንደር የሰቀልት አይምባ አካባቢ ነዋሪ የሆነው ፋኖ አይሸሽም ዮሃንስ ከአማራ ሚዲያ ማዕከል ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ቆይታ አድርጓል። ፋኖ አይሸሽም እንዳለው መንግስት ቀደም ብሎ የፋኖ አደረጃጀትን መጠቀም ቢችል ኖሮ በፀጥታ መዋቅሩ ላይ በፅንፈኞችና አገር አፍራሾች በኩል የሚደርሱ ጉዳቶችን መቀነስ ይችል እንደነበር ጠቅሷል። ፋኖ ትናንትም ዛሬም ሲጠይቀው የነበረውን ጥያቄ ለመመለስ ከመከላከያ ሰራዊትና ከልዩ ሀይላችን ጎን በመሆን ያደረገው ተጋድሎ የሚደነቅና ሊመሰገን የሚገባው ነገር ነው ሲልም አክሏል። ፋኖ የሚሰራው ወይም የሚደራጀው እንደሌሎች አገር ለማፍረስ ሳይሆን ለመኖር፣ አገር እንደአገር እንድትቀጥል ነው ያለው ፋኖ አይሸብም ለዚህም ከ2010 እስካሁን ባለው ትግል ህዝብ ምስክር ነው ብሏል። ዛሬም ነገም ፋኖ አለ፤ አገር ሰላም እስክትሆን ድረስ ይቀጥላል፤ ይህን ፋኖ ማፍረስ ማለት አማራን ማፍረስ ነው ሲልም ተናግሯል። ይህን በውል ያልተረዱ የመንግስት አመራሮች ፋኖን እንደ ሽፍታ መመልከት ከተሳሳተው የሕወሓት የጁንታ ቡድን አጀንዳ የተወሰደ ነው እንጅ እውነት ከማንም ሰው ሆኖ ከሚያስብ የአማራ ክልል ወኪል/መሪ አንደበት የሚመጣ እንዳልነበር ለመረዳት ይቻላል ሲልም አክሏል። ላለፉት በርካታ ዓመታት ያ ሁሉ ግፍና በደል የደረሰው ጠንካራ አደረጃጀት ባለመኖሩ፣ በአማራ ክልል ላይ መደራጀት ማለት እንደ ወንጀል ሆኖ መቆጠሩ ስለመሆኑ የገለፀው ፋኖ አይሸሽም ሌሎች ለጥፋት አገር ለመበተን ይደራጃሉ እኛ ደግሞ ራሳችንና አካባቢያችን ለመጠበቅ ስንደራጅ የነበረብን ተፅዕኖ መደገም የለበትም ነው ያለው። የፀጥታ አካሉ የየአካባቢውን ህብረተሰብ በማሳተፍ ራሱንና አካባቢውን መጠበቅ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ያሳሰበው ፋኖው መሪዎች ወክለነዋል ያሉትን ህዝብ መፍራት የለባቸውም፤ ጦር መሳሪያ ባነገቡ መታጀብ የለባቸውም፣ አሳታፊ የሆነ አሰራርን እንዲከተሉም መክሯል። በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ ወገኖች ሊመሰገኑ ይገባል ምክንያቱም የትጥቅ፣የስምሪትና የስንቅ እንዲሁም የስነ ልቦና በሞራል ግንባታው ረገድ የነቃ ተሳትፎ ነበራቸው፣ ይህም ከታጠቀው ሀይል የበለጠ ረድቶናል ብሏል። ሌሎች ሀገር ለማፍረስ ገንዘብ ሲያሰባስቡ የእኛ ወንድሞች ደግሞ ገንዘብ የሚያሰባስቡት አገር እንዳትፈርስ፣አገር አንድ እንድትሆን፣ ህዝቡ በሀገሩ፣ አማራው በራሱ መሬት በኢትዮጵያ ምድር የትም ቦታ ተንቀሳቅሶ እንዲኖር ነው ብሏል_ ፋኖ አይሸሽም። በመጨረሻም የህወሀት ቡድን ቢደመሰስም ሌሎች የእነሱ ተከታዮች ቅርንጫፎች ስላሉ መንግስትና ህዝቡ በመተባበር መታገል አለበት፣ የመኖር ያለመኖር ጉዳይ ስለሆነ እንሳተፍ፣ መተኛት የለብንም፣በህወሐት ላይ የተወሰደው እርምጃ መተከል ላይ ባሉ ጁንታዎችም መወሰድ አለበት ሲልም ጥሪ አድርጓል። በድምፅ የተደገፈ ሙሉ ቆይታችን በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይከታተሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply